عَنْ أَبِي سَعِيدٍ الْخُدْرِيِّ رَضيَ اللهُ عنهُ عَنِ النَّبِيِّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ قَالَ:
«إِنَّ فِي الْجَنَّةِ شَجَرَةً يَسِيرُ الرَّاكِبُ الْجَوَادَ الْمُضَمَّرَ السَّرِيعَ مِائَةَ عَامٍ مَا يَقْطَعُهَا».
[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح مسلم: 2828]
المزيــد ...
ከአቡ ሰዒድ አልኹድሪይ ረዲየሏሁ ዐንሁ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: ነቢዩ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - እንዲህ ብለዋል፦
"ጀነት ውስጥ ዛፍ አለች። ረጅም ጊዜ የተቀለበችና ፈጣን የሆነችን ፈረስ ምርጥ ጋላቢ መቶ አመት ጋልቦ ይህቺን ዛፍ አያቋርጣትም።"
[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 2828]
ነቢዩ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ጀነት ውስጥ ዛፍ እንዳለና ለውድድር የተዘጋጀንና ሲሮጥ ፈጣን የሆነን ፈረስ የሚጋልብ ሰው በዛፉ ስር መቶ አመት ጋልቦም የመጨረሻ ቅርንጫፉ ጋር እንደማይደርስ ተናገሩ።