عَنْ عَبْدِ اللهِ بْنِ عَمْرٍو رَضيَ اللهُ عنهما قَالَ:
رَجَعْنَا مَعَ رَسُولِ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ مِنْ مَكَّةَ إِلَى الْمَدِينَةِ حَتَّى إِذَا كُنَّا بِمَاءٍ بِالطَّرِيقِ تَعَجَّلَ قَوْمٌ عِنْدَ الْعَصْرِ، فَتَوَضَّؤُوا وَهُمْ عِجَالٌ، فَانْتَهَيْنَا إِلَيْهِمْ وَأَعْقَابُهُمْ تَلُوحُ لَمْ يَمَسَّهَا الْمَاءُ فَقَالَ رَسُولُ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ: «وَيْلٌ لِلْأَعْقَابِ مِنَ النَّارِ أَسْبِغُوا الْوُضُوءَ».
[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح مسلم: 241]
المزيــد ...
ከዐብደላህ ቢን ዐምር (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ:
«ከአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ጋር ከመካ ወደ መዲና ተመለስን። ውሃ የሚገኝበት መንገድ ላይ የደረስን ጊዜ ሰዎች ዐስርን በወቅቱ ለመስገድ በመቻኮል ፈጥነው ዉዱእ አደረጉ። ወደነርሱም ተረከዞቻቸው ውሃ ያልነካው ግልፅ ሆኖ ደረስንባቸው። በዚህ ወቅትም የአላህ መልክተኛም (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ አሉ " ተረከዞቻችሁን ከእሳት አድኑ! ዉዱእን አዳርሳችሁ አድርጉ!"»
[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 241]
ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ባልደረቦቻቸው ጋር ሆነው ከመካ ወደ መዲና እየተጓዙ ሳለ መንገዳቸው ላይ ውሃ አገኙ። ከፊል ሶሐቦችም ዐስርን ለመስገድ ዉዱእ በማድረግ ተቻኮሉ። ከመቻኮላቸውም የተነሳ ተረከዞቻቸው ደረቅ እንደሆነና ውሃ እንዳልነካው ለተመልካችም በግልፅ ያስታውቅ ነበር። ነቢዩም (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ዉዱእ በሚያደርጉ ወቅት የእግራቸውን ተረከዝ ከመታጠብ ችላ ለሚሉ ሰዎች የእሳት ውስጥ ቅጣትና ጥፋት እንዳለባቸው ተናገሩ። ዉዱእን አሟልቶ በመፈፀም ላይ ከፍተኛ ጥረት እንዲያደርጉም አዘዟቸው።