ምድቡ:
+ -

عَنْ أَبِي ثَعْلَبَةَ الخُشَنِيِّ جُرْثُومِ بن نَاشِرٍ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُ عَنْ رَسُولِ اللَّهِ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ قَال:
«إِنَّ اللَّهَ فَرَضَ فَرَائِضَ فَلَا تُضَيِّعُوهَا، وَحَدَّ حُدُودًا فَلَا تَعْتَدُوهَا، وَحَرَّمَ أَشْيَاءَ فَلَا تَنْتَهِكُوهَا، وَسَكَتَ عَنْ أَشْيَاءَ رَحْمَةً لَكُمْ غَيْرَ نِسْيَانٍ فَلَا تَبْحَثُوا عَنْهَا».

[قال النووي: حديث حسن] - [رواه الدارقطني في سننه، وغيره] - [الأربعون النووية: 30]
المزيــد ...

ከአቡ ሠዕለባ አልኹሸኒይ ጁርሡም ቢን ናሺር -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው የአላህ መልክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን እንዲህ ብለዋል:
"አላህ ግዴታዎችን ደነግጓል። (ባለመስራት) አታጥፏት። ድንበሮችን ወስኗል። አትተላለፏት። ነገሮችን ከልክሏል አትዳፈሯት። ለናንተው በማዘን ሳይረሳው አንዳንድ ነገሮችንም ዝም ብሏል፤ ስለርሷ አትፈላፈሉ።"

[قال النووي: حديث حسن] - [رواه الدارقطني في سننه وغيره] - [الأربعون النووية - 30]

ትንታኔ

ነቢዩ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- እንዲህ በማለት ተናገሩ። አላህ ብዙ ነገሮችን ግዴታ አድርጓልም ደንግጓልም። አጥብቃችሁ ያዙት፤ በመተው ወይም በመዘናጋት እንዳታጓድሉት። አላህ እናንተን የሚያቅቡና እርሱ ከማይወደው የሚያግዷችሁን የተወሰኑ ማቀቢያዎችንና ማገጃዎችን አድርጓልና በሸሪዓ ካዘዘው አትለፉ። አላህ ውግዝ ነገሮችን ስለከለከለ አትፈፅሟትም አትቅረቧትም። ከነዚህ ውጪ ያሉን ግን ለባሮቹ በማዘን ትቷቸዋል ዝምም ብሏቸዋል። ልክ በመሰረቱ እንደነበረው ፍቁድ እንደሆነ ይቀራል። ስለርሱም አትፈላፈሉ።

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. ይህ ሐዲሥ አላህ ብቻ ህግ ደንጋጊ እንደሆነና ነገሮች በእጁ እንደሆኑ ይጠቁማል።
  2. ይህ ሐዲሥ በመፍረድም ይሁን በመፍቀድ ረገድ የሸሪዓን መርሆዎች ያካተተ ሐዲሥ ነው። ምክንያቱም ሸሪዓዊ ብይን: ወይ ዝም የተባለ ነው ወይም የተዘረዘረ ነው። የተዘረዘረ የሸሪዓ ብይን ወይ በግዴታነትም ይሁን በተወዳጅነት የታዘዘ ነው፤ ወይም በእርምነት (ክልክልነት) ደረጃም ይሁን በውግዝነት የተከለከለ ነው፤ ወይም ደሞ የተፈቀደ ነው።
  3. አላህ ግዴታ ሳያደርገው፣ ገደብ ሳያበጅለት፣ ሳይከለክለው በዝምታ ያለፈው ነገር ፍቁድ ነው።
  4. ነቢዩ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- በዚህ ግልፅና ፍንትው ባለ መልኩ ሐዲሡን መዘርዘራቸው ውብ የሆነ የማብራራት ብቃት እንዳላቸው ያስረዳናል።
  5. አላህ ግዴታ ያደረጋቸውን ነገሮች መጠባበቅ ግዴታ መሆኑን እንረዳለን።
  6. የአላህን ድንበሮች መተላለፍ ክልክል መሆኑን እንረዳለን።
ትርጉም: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ኢንዶኔዥያኛ ባንጋሊኛ ቱርክኛ ሩስያኛ ቦስንያኛ ሲንሃላዊ ህንድኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ቬትናማዊ ታጋሎግ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ማላያላምኛ ቴልጉ ስዋሒልኛ ታሚልኛ ታይላንድኛ ጀርመንኛ ቡሽትኛ አሳምኛ አልባንኛ الهولندية الغوجاراتية Kyrgyzisht النيبالية الليتوانية الدرية الصربية الطاجيكية Kinjaruandisht المجرية التشيكية الموري Malagasisht Kannadisht الولوف Azerisht الأوزبكية الأوكرانية الجورجية المقدونية الخميرية الماراثية
ትርጉሞችን ይመልከቱ
ምድቦች
ተጨማሪ