ምድቡ:
+ -

عَنْ أَمِيرِ المُؤْمِنِينَ أَبِي حَفْصٍ عُمَرَ بْنِ الخَطَّابِ رضي الله عنه قَالَ: سَمِعْتُ رَسُولَ اللَّهِ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ يَقُولُ:
«إنَّمَا الأَعْمَالُ بِالنِّيَّاتِ، وَإِنَّمَا لِكُلِّ امْرِئٍ مَا نَوَى، فَمَنْ كَانَتْ هِجْرَتُهُ إلَى اللَّهِ وَرَسُولِهِ فَهِجْرَتُهُ إلَى اللَّهِ وَرَسُولِهِ، وَمَنْ كَانَتْ هِجْرَتُهُ لِدُنْيَا يُصِيبُهَا أَوْ امْرَأَةٍ يَنْكِحُهَا فَهِجْرَتُهُ إلَى مَا هَاجَرَ إلَيْهِ».

[صحيح] - [رواه إماما المحدثين أبو عبد الله محمد بن إسماعيل بن إبراهيم بن المغيرة بن بردزبه البخاري، وأبو الحسين مسلم بن الحجاج بن مسلم القشيري النيسابوري في صحيحيهما اللذين هما أصح الكتب المصنفة] - [الأربعون النووية: 1]
المزيــد ...

ከአሚረል ሙእሚኒን (ከምእመናን መሪ) አቡ ሐፍስ ዑመር ኢብኑል ኸጧብ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና - በተላለፈ ሐዲሥ እንዲህ ብለዋል፡- «የአላህ መልክተኛን የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን እንዲህ ሲሉ ሰምቻለሁ፡-
"ስራዎች (ተቀባይነታቸው የሚለካው) በኒያ ብቻ ነው። ማንኛውም ሰው የሚመነዳውም ባለመው ኒያ ልክ ብቻ ነው። ስደቱ ወደ አላህና ወደ መልዕክተኛው ብሎ የሆነ ሰው (ምንዳውም) ለአላህና ለመልእክተኛው ሆኖለታል፤ የዱንያን ጥቅም ለማግኘት ወይም ሴትን ለማግባት ብሎ የተሰደደ ሰውም የስደቱ (ምንዳ) ለተሰደደለት ጉዳይ ነው።"»

[ሶሒሕ ነው።] - [رواه إماما المحدثين أبو عبد الله محمد بن إسماعيل بن إبراهيم بن المغيرة بن بردزبه البخاري وأبو الحسين مسلم بن الحجاج بن مسلم القشيري النيسابوري في صحيحيهما اللذين هما أصح الكتب المصنفة] - [الأربعون النووية - 1]

ትንታኔ

ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ሁሉም ስራዎች ግምት የሚሰጣቸው በኒያ እንደሆነ አብራሩ። ይህ ብይን በአምልኳዊም ጉዳይ ሆነ ከሰው ጋር ባሉ መስተጋብሮች ሁሉንም ስራዎች የሚያጠቃልል ነው። በስራው የሆነን ጥቅም ያሰበ ሰው ከዛች ጥቅም በስተቀር ሌላ አያገኝም። ምንዳም የለውም። በስራው ወደ አላህ መቃረብን ያሰበ ሰው ደግሞ እንደ መብላትና መጠጣት የመሰሉ ተለምዷዊ ስራ ቢሆንም እንኳ ሰርቶ በስራው ምንዳና አጅርን ያገኛል።
ቀጥለውም ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ስራዎች በውጫዊ ይዘታቸው ሲታዩ ተመሳሳይ ከመሆናቸውም ጋር ኒያ በስራዎች ላይ የሚያሳድረውን ተፅእኖ ለማብራራት ምሳሌ ጠቀሱ። በስደቱና ሀገሩን በመተዉ የአላህን ውዴታ ማግኘትን ያሰበ ስደቱ ሸሪዐዊና ተቀባይነት ያለው ስደት ነው። ኒያው እውነተኛ ስለሆነም ይመነዳበታል። በስደቱ ግን እንደ ገንዘብ፣ ክብር፣ ንግድና ሚስት የመሳሰሉ ዓለማዊ ጥቅም የፈለገ ሰው ከስደቱ ይህችን ያሰባትን ጥቅም በስተቀር ሌላ አያገኝም። ከምንዳና አጅርም ምንም እጣ ፈንታ እንደሌለው ገለፁ።

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. አላህ የሱ ፊት ተፈልጎበት የተሰራን ስራ ካልሆነ በስተቀር ምንም ስራ አይቀበልምና በኢኽላስ ላይ መበረታታቱን እንረዳለን።
  2. አንድ ሸሪዓዊ ብይኖች የሚመለከቱት ዕድሜ ክልል ላይ የደረሰ ሰው ወደ አላህ የሚቃረብበትን ስራ በተለምዷዊ እሳቤ ቢሰራው በስራው ወደ አላህ መቃረብን እስኪያስብ ድረስ በሷ አማካኝነት ምንም ምንዳ አይኖረውም።
  3. አምልኮዎች አንዱ ከአንዱ የሚለዩትም ይሁን አምልኮዎች ከተለምዶ የሚለዩት በኒያ ነው።
ትርጉም: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ኢንዶኔዥያኛ ባንጋሊኛ ቱርክኛ ሩስያኛ ቦስንያኛ ሲንሃላዊ ህንድኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ቬትናማዊ ታጋሎግ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ማላያላምኛ ቴልጉ ስዋሒልኛ ታሚልኛ ታይላንድኛ ጀርመንኛ ቡሽትኛ አሳምኛ አልባንኛ الغوجاراتية Kyrgyzisht النيبالية الدرية الصربية الطاجيكية Kinjaruandisht المجرية التشيكية الموري Kannadisht الولوف Azerisht الأوزبكية الأوكرانية الجورجية المقدونية الخميرية
ትርጉሞችን ይመልከቱ
ምድቦች
ተጨማሪ