عَنْ حُمْرَانَ مَوْلَى عُثْمَانَ بْنِ عَفَّانَ رضي الله عنه:
أَنَّهُ رَأَى عُثْمَانَ بْنَ عَفَّانَ دَعَا بِوَضُوءٍ، فَأَفْرَغَ عَلَى يَدَيْهِ مِنْ إِنَائِهِ، فَغَسَلَهُمَا ثَلَاثَ مَرَّاتٍ، ثُمَّ أَدْخَلَ يَمِينَهُ فِي الْوَضُوءِ، ثُمَّ تَمَضْمَضَ وَاسْتَنْشَقَ وَاسْتَنْثَرَ، ثُمَّ غَسَلَ وَجْهَهُ ثَلَاثًا، وَيَدَيْهِ إِلَى الْمِرْفَقَيْنِ ثَلَاثًا، ثُمَّ مَسَحَ بِرَأْسِهِ، ثُمَّ غَسَلَ كُلَّ رِجْلٍ ثَلَاثًا، ثُمَّ قَالَ: رَأَيْتُ النَّبِيَّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ يَتَوَضَّأُ نَحْوَ وُضُوئِي هَذَا، وَقَالَ: «مَنْ تَوَضَّأَ نَحْوَ وُضُوئِي هَذَا ثُمَّ صَلَّى رَكْعَتَيْنِ لَا يُحَدِّثُ فِيهِمَا نَفْسَهُ غَفَرَ اللهُ لَهُ مَا تَقَدَّمَ مِنْ ذَنْبِهِ».
[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح البخاري: 164]
المزيــد ...
በዑሥማን ነፃ የወጣ የሆነው ሑምራን እንዳስተላለፈው እሱ "ዑሥማንን የውዱእ እቃ እንዲያመጡላቸው ሲጣሩ አየ። (የውዱእ እቃ ሲቀርብላቸውም) ከእቃው ውሀ በእጆቻቸው ላይ አፈሰሱ። እያፈሰሱም ሶስት ጊዜ አጠቧቸውቸው። ከዚያም ቀኝ እጃቸውን በውዱእ እቃ ውስጥ አስገብተው ውሀ ዘገኑና በዚያው ተጉመጠመጡ አፍንጫቸው ውስጥም ውሀውን አስገብተው ድጋሚ አስወጡ። ከዚያም ፊታቸውን ሶስት ጊዜ፣ ሁለት እጆቻቸውንም እስከ ክርኖቻቸው ሶስት ጊዜ አጠቡ። ከዚያም ጭንቅላታቸውን አበሱ። ከዚያም ሁለት እግሮቻቸውን ሶስት ጊዜ አጠቡ። ከዚያም እንዲህ አሉ 'ነቢዩን ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም በዚህ መልኩ ውዱእ ሲያደርጉ ተመልክቻቸዋለሁ። ከዚያም 'እኔ እንዳደረጉት አይነት ዉዱእ አድርጎ ከዚያም ነፍሱን ምንም በሃሳብ ሳያደፈርስ ሁለት ረከዐ የሰገደ ሰው ያሳለፈው ወንጀሉ ተምሮለታል።' አሉ።'"
[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ አልቡኻሪ - 164]
ዑሥማን (ረዺየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - የነቢዩን (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ዉዱእ አደራረግ እጅግ በጣም የተብራራ እንዲሆን ተግባራዊ በሆነ መንገድ አስተማሩ። በውዱእ እቃ ውሀ እንዲያመጡላቸው ጠየቁ። ቀጥሎም በእጆቻቸው ላይ ሶስት ጊዜ አፈሰሱ። ከዚያም ቀኝ እጃቸውን እቃ ውስጥ ከተው ውሀ በማውጣት ውሀውን አፉቸው ውስጥ ከተው ካመላለሱ በኋላ ተፉት። ቀጥሎም ውሀውን ወደ አፍንጫቸው ውስጥ ከሳቡ በኋላ መልሰው አወጡት። ከዚያም ፊታቸውን ሶስት ጊዜ አጠቡ። ከዚያም እጃቸውን ከክርናቸው ጋር ሶስት ጊዜ አጠቡ። ከዚያም እጃቸውን አርጥበው ጭንቅላታቸው ላይ አንድ ጊዜ አበሱ። ከዚያም ሁለት እግሮቻቸውን ከቁርጭምጭሚታቸው ጋር ሶስት ጊዜ አጠቡ።
ዑሥማን (ረዲየላሁ ዐንሁ) -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና- ዉዱአቸውን ባጠናቀቁ ጊዜ ነቢዩን (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) በዚህ መልኩ ዉዱእ ሲያደርጉ እንደተመለከቱና በዚህ መልኩ ዉዱእ አድርጎ ልቡንም ጌታው ዘንድ ጥዶ በተመስጦ ሁለት ረከዐ የሰገደ ሰው አላህ በዚህ የተሟላ ዉዱእና የጠራ ሶላት ምክንያት ያለፈውን ወንጀሉ በመማር እንደሚመነዳው እንዳበሰሯቸው ነገሯቸው።