+ -

عَنْ أُمِّ عَطِيَّةَ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهَا قَالَتْ:
نُهِينَا عَنِ اتِّبَاعِ الجَنَائِزِ، وَلَمْ يُعْزَمْ عَلَيْنَا.

[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح البخاري: 1278]
المزيــد ...

ከኡሙ ዐጢየህ - አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና - እንደተላለፈው እንዲህ አለች:
"ጀናዛን ከመሸኘት ተከልክለናል። አፅንዖት ሰጥተው ግን አልከለከሉንም።"

[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ አልቡኻሪ - 1278]

ትንታኔ

ኡሙ ዐጢየህ አልአንሷሪየህ (አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና) ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ሴቶች ጀናዛን ለመሸኘት አብረው ከመሄድ እንደተከለከሉ ተናገረች። ይህም ለነርሱም ይሁን በነርሱ ምክንያት ፈተና ይከሰታል ተብሎ ስለተፈራና ትእግስታቸው ያነሰ ስለሆነ ነው። ቀጥላም (አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና) ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ሌሎች ክልከላዎች ላይ እንደሚያከብዱት ይህንን ግን ክብደት ሰጥተው አልከለከሉም አለች።

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. ሴቶች ጀናዛን ከመሸኘት መከልከላቸውን እንረዳለን። ይህም ጀናዛው ወደሚሰናዳበትም ወደሚሰገድብትም ይሁን ወደ መቃብር ስፍራ ሲሄድ ያለውን መከተል ሁሉ የሚያካትት ክልከላ ነው።
  2. የክልከላው ምክንያትም ሴቶች እንደዚህ አይነት የሚያሳዝን ሁኔታዎችና ልብ የሚነካ አጋጣሚዎችን መቋቋም ስለማይችሉ በዚህም ሰበብ ምንአልባት ግዴታቸው የሆነውን ትእግስት የሚፃረር ማማረርና ትእግስት ማጣት ሊታይባቸው ስለሚችል ነው።
  3. ክልከላ በመሰረቱ እርምነትን (ሐራምነትን) ነው የሚጠቁመው። ነገር ግን ኡሙ ዐጢየህ (አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና) በጊዜው ከነበረው የአነጋገር ሁኔታ ጀናዛን ከመሸኘት መከልከላቸው አፅንዖት የተሰጠው ቁርጥ ክልከላ እንዳልሆነ ተረዳች። ነገር ግን ጀናዛን የመሸኘት ክልከላው ጠንከር ያለ መሆኑን የሚጠቁሙ ይህ ሐዲሥ ከሚጠቁመው የበለጠ በርካታ ሐዲሦች መጥተዋል።
ትርጉም: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ስፔንኛ ኢንዶኔዥያኛ ኡይጙራዊ ባንጋሊኛ ፈረንሳይኛ ቱርክኛ ሩስያኛ ቦስንያኛ ሲንሃላዊ ህንድኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ቬትናማዊ ታጋሎግ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ስዋሒልኛ ታይላንድኛ አሳምኛ الدرية الرومانية المجرية الجورجية الخميرية الماراثية
ትርጉሞችን ይመልከቱ