عَنْ عَبْدِ اللَّهِ بْنِ مَالِكٍ ابْنِ بُحَيْنَةَ رضي الله عنه:
أَنَّ النَّبِيَّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ كَانَ إِذَا صَلَّى فَرَّجَ بَيْنَ يَدَيْهِ حَتَّى يَبْدُوَ بَيَاضُ إِبْطَيْهِ.
[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح البخاري: 390]
المزيــد ...
ከዐብደላህ ቢን ማሊክ ኢብኑ ቡሐይና (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ:
ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) በሚሰግዱ ጊዜ የብብታቸው ንጣት ግልፅ እስኪሆን ድረስ በእጆቻቸው መካከል ይከፍቱ ነበር።
[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ አልቡኻሪ - 390]
ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ሱጁድ በሚያደርጉ ወቅት በእጆቻቸው መካከል ይከፍቱ ነበር። የሁለቱም ብብታቸው የቆዳ ቀለም ግልፅ እስኪሆን ድረስ ሁሉንም የእጃቸውን ክፍል እንደክንፍ ከጎናቸው ያርቁት ነበር። ይህ ድርጊታቸው ክንዳቸውን ከጎናቸው ምን ያህል እንደሚያርቁ የሚያሳይ ነው።