عَن أُمِّ الدَّرْدَاءِ وَ أَبِي الدَّرداءِ رَضيَ اللهُ عنهما أَنَّ النَّبِيَّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ كَانَ يَقُولُ:
«دَعْوَةُ الْمَرْءِ الْمُسْلِمِ لِأَخِيهِ بِظَهْرِ الْغَيْبِ مُسْتَجَابَةٌ، عِنْدَ رَأْسِهِ مَلَكٌ مُوَكَّلٌ كُلَّمَا دَعَا لِأَخِيهِ بِخَيْرٍ، قَالَ الْمَلَكُ الْمُوَكَّلُ بِهِ: آمِينَ وَلَكَ بِمِثْلٍ».
[صحيح] - [رواه مسلم] - [صحيح مسلم: 2733]
المزيــد ...
ከኡሙ ደርዳ እና ከአቡ ደርዳእ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ይሉ ነበር:
«አንድ ሙስሊም ሰው ለወንድሙ ከሩቅ (በሌለበት) የሚያደርግለት ዱዓ ተቀባይነት አለው። ከጭንቅላቱ በላይ የተወከለ መልአክ አለ። ለወንድሙ መልካም ነገርን ዱዓ ባደረገለት ቁጥር ለዚህ ጉዳይ የተወከለው መልአክም "አሚን ላንተም ተመሳሳዩ አለህ።" ይለዋል።»
[ሶሒሕ ነው።] - [ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 2733]
ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በርሳቸው ላይ ይስፈንና) ሙስሊም የሆነ ሰው ለሙስሊም ወንድሙ ከሩቅ ‐ ዱዓ የሚደረግለት ሰው በሌለበት ‐ የሚያደርገው ዱዓ ተቀባይነት እንዳለው ተናገሩ። ይህም የኢኽላስ ጥግ የደረሰ ዱዓ ስለሆነ ነው። ዱዓ አድራጊው ጭንቅላት ዘንድም የተወከለ መልአክ እንዳለና ለወንድሙ መልካም ነገርን ዱዓ ባደረገ ቁጥር ለዚህ ጉዳይ የተወከለው መልአክ "አሚን ላንተም ዱዓ ያደረግከውን አምሳያ ይስጥህ።" እንደሚልም ተናገሩ።