عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ رَضيَ اللهُ عنهُ أَنَّ رَسُولَ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ قَالَ:
«رُبَّ أَشْعَثَ مَدْفُوعٍ بِالْأَبْوَابِ لَوْ أَقْسَمَ عَلَى اللهِ لَأَبَرَّهُ».
[صحيح] - [رواه مسلم] - [صحيح مسلم: 2622]
المزيــد ...
ከአቡ ሁረይራ ረዲየሏሁ ዐንሁ -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: «የአላህ መልክተኛ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- እንዲህ ብለዋል፦
"ፀጉረ ጨብራራና ከበር ተገፍትሮ የሚባረር በአላህ ሲምል ግን አላህ ከመሃላው የሚያጠራው ስንትና ስንት ሰው አለ?!"
[ሶሒሕ ነው።] - [ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 2622]
ነቢዩ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ከሰዎች መካከል ፀጉሩ አመዳም የሆነና የተቆጣጠረ፤ ቅባትም የማይቀባውና አብዝቶ የማይታጠበው፤ ሰዎች ዘንድ ቦታ ስለሌለው አሳንሰውም ስለሚያዩት ከበራቸው የሚገፈትሩትና የሚያባሩት አይነት ሰው እንዳለ ነገር ግን ይህ ሰው አንድ ነገር እንደሚከሰት ቢምል መሃላው እንዳይፈርስና በዛም ተጠያቂነት እንዳይመጣበት አላህ እርሱን በማክበር መሃላውን ከማፍረስ ሊታደገው ዘንድ ጉዳዩን ተቀብሎ የማለበት ነገር እንዲከሰት የሚያደርግለት ሰው ነው። ይህም አላህ ዘንድ ደረጃና ክብር ስላለው መሆኑን ብለው ተናገሩ።