عن عُمر بن أبي سلمة رضي الله عنه قال:
كُنْتُ غُلَامًا فِي حَجْرِ رَسُولِ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ، وَكَانَتْ يَدِي تَطِيشُ فِي الصَّحْفَةِ، فَقَالَ لِي رَسُولُ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ: «يَا غُلَامُ، سَمِّ اللهَ، وَكُلْ بِيَمِينِكَ، وَكُلْ مِمَّا يَلِيكَ» فَمَا زَالَتْ تِلْكَ طِعْمَتِي بَعْدُ.

[صحيح] - [متفق عليه]
المزيــد ...

ከዑመር ቢን አቢ ሰለማህ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ:
"በአላህ መልዕክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ጎጆ ውስጥ የምኖር ህፃን ልጅ ነበርኩ። በማዕዱ ላይም እጄ ትሽከረከር ነበር። የአላህ መልዕክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ለኔ እንዲህ አሉኝ ' አንተ ልጅ ሆይ! ቢስሚላህ በል! በቀኝህ ብላ፣ ፊትህ ካለውም ብላ!' ከዚያን ጊዜ በኋላ ከዚህ የአበላል ስርአት አልተወገድኩም።"

Sahih/Authentic. - [Al-Bukhari and Muslim]

ትንታኔ

ዑመር ቢን አቢ ሰለማህ (ረዲየላሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና የነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ባለቤት የሆነችው የኡሙ ሰለማህ ልጅ ነው። በሳቸው እነፃና እንክብካቤ ስር ነበር። በሚበላበት ወቅት ምግብ ለማንሳት እጁን በእቃው ዙሪያ ያዘዋውር ነበር። ነቢዩም (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ሶስት የአመጋገብ ስርአቶችን አስተማሩት:
የመጀመሪያው: መብላት ሲጀመር "ቢስሚላሂ" ማለት ነው።
ሁለተኛው: በቀኝ መብላት ነው።
ሶስተኛው: ለርሱ ቅርብ በሆነ ምግብ በኩል መመገብ ነው።

ትርጉም: እንግሊዝኛ ፈረንሳይኛ ስፔንኛ ቱርክኛ የኡርዱ ቋንቋ ኢንዶኔዥያኛ ቦስንያኛ ሩስያኛ ባንጋሊኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ህንድኛ ቬትናማዊ ሲንሃላዊ ኡይጙራዊ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ማላያላምኛ ቴልጉ ስዋሒልኛ ታሚልኛ ቦርምኛ ታይላንድኛ ጃፓንኛ ቡሽትኛ አሳምኛ አልባንኛ السويدية الهولندية الغوجاراتية الدرية
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. ከመብላትና መጠጣት ስርአቶች መካከል መጀመሪያ ቢስሚላህ ማለት አንዱ ነው።
  2. ህፃናትን ስርአት ማስተማር እንደሚገባ በተለይ በሰውዬው ሀላፊነት ስር ያለን ልጅ ስርአት ማስተማር እንደሚገባ እንረዳለን።
  3. ህፃናትን በማስተማርና ስርአት በማስያዙ ረገድ የነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እዝነትና ልበ ሰፊነትን እንረዳለን።
  4. ከፊቱ ካለው መመገብ ከአመጋገብ ስርአቶች መካከል አንዱ ነው። የምግብ አይነቶቹ ብዙ የሆኑ ጊዜ ግን ከፊቱ ውጪ ካለ መውሰድም ይችላል።
  5. ሶሐቦች ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ያስተማሯቸውን ስርአት አጥብቀው መያዛቸውን እንረዳለን። ይህንንም ነጥብ "ከዛን ጊዜ በኋላ ከዚህ የአበላል ስርአት አልተወገድኩም።" ከሚለው የዑመር ንግግር እንረዳለን።