عَنْ أَبِي سَعِيدٍ الْخُدْرِيِّ رضي الله عنه قَالَ: قَالَ رَسُولُ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ:
«لَتَتَّبِعُنَّ سَنَنَ الَّذِينَ مِنْ قَبْلِكُمْ، شِبْرًا بِشِبْرٍ، وَذِرَاعًا بِذِرَاعٍ، حَتَّى لَوْ دَخَلُوا فِي جُحْرِ ضَبٍّ لَاتَّبَعْتُمُوهُمْ» قُلْنَا: يَا رَسُولَ اللهِ آلْيَهُودَ وَالنَّصَارَى؟ قَالَ: «فَمَنْ؟».
[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح مسلم: 2669]
المزيــد ...
ከአቡ ሰዒድ አልኹድሪይ (ረዲየላሁ ዐንሁ) -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንዲህ አሉ፦ «የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል፦
"ከናንተ በፊት የነበሩትን (ሕዝቦች) ጎዳና ስንዝር በስንዝር፣ ክንድ በክንድ ትከተላላችሁ። የወከሎ ቤት (ጉድጓድ) ቢገቡ እንኳ ትከተሏችኋላችሁ።" እኛም "የአላህ መልክተኛ ሆይ! ክርስቲያኖችንና አይሁዶችን ነውን?" አልናቸው። እርሳቸውም "ታዲያ ሌላ ማን ነው?" አሉን።»
[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 2669]
ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ከርሳቸው ዘመን በኋላ የአንዳንድ ኡመታቸው ሁኔታ እንዴት እንደሚሆን ተናገሩ። እርሱም የአይሁዶችንና የክርስቲያኖችን መንገድ በእምነታቸው፣ በድርጊታቸው፣ በልማዳቸውና ባህላቸው እጅግ በረቀቀ መንገድ ስንዝር በስንዝር፣ ክንድ በክንድ መከተል ነው። የወከሎ ቤት ቢገቡ እንኳ እነሱም ከኋላቸው ተከትለዋቸው ይገባሉ።