عن ابنِ عُمَرَ رضي الله عنهما قال: قال رسولُ الله صلَّى الله عليه وسلم:
«مَن تَشَبَّهَ بِقَوْمٍ فَهُوَ مِنْهُمْ».

[حسن] - [رواه أبو داود وأحمد] - [سنن أبي داود: 4031]
المزيــد ...

ከኢብኑ ዑመር -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አለ: የአላህ መልክተኛ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ አሉ:
"ከህዝቦች ጋር የተመሳሰለ እርሱ ከነርሱው ይመደባል።"

[ሐሰን ነው።] - [አቡዳውድና አሕመድ ዘግበውታል።] - [ሱነን አቡዳውድ - 4031]

ትንታኔ

የነርሱ መለዮ የሆነን እምነት ወይም አምልኮ ወይም ተለምዷዊ ነገርን በማድረግ ከከሀዲያን ወይም ከአመፀኞች ወይም ከደጋግ ህዝቦችም ጋር የተመሳሰለ ሰው ከነርሱ እንደሚመደብ ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ተናገሩ። ምክንያቱም በውጫዊ ማንነት ከነርሱ ጋር መመሳሰል በውስጣዊ ማንነት ከነርሱ ጋር ወደ መመሳሰል ያደርሳልና። ከሆኑ ህዝቦች ጋር መመሳሰል በነሱ የመደነቅ ውጤት መሆኑ ጥርጥር የሌለው ጉዳይ ነው። ቀስ በቀስም እነሱን ወደመውደድ ፣ ወደማላቅ፣ ወደነርሱ ጥገኛ ወደመሆን ያደርሳል። ይህም አላህ ይጠብቀንና ሰውዬውን በውስጣዊ አመለካከቱና አምልኮው ሳይቀር ከነርሱ ጋር ወደመመሳሰል ይጎትተዋል።

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. ከከሀዲያንና አመፀኛ ህዝቦች ጋር መመሳሰል መከልከሉን እንረዳለን።
  2. ከደጋጎች ጋር መመሳሰልና እነሱን መከተል መበረታታቱን እንረዳለን።
  3. በውጫዊ ማንነት መመሳሰል በውስጥ መውደድን እንደሚያወርስ እንረዳለን።
  4. ሰውዬው በተመሳሰለው ልክና አይነት ወንጀልና ዛቻ እንደሚያጋጥመው እንረዳለን።
  5. ከከሀዲያን ጋር እነሱ የተለዩበት በሆኑ እምነታቸውና ተለምዷቸው መመሳሰል መከልከሉን እንረዳለን። ይህ ባልሆነበት የተለያዩ ሙያዎችን መማርና የመሳሰሉት ግን ክልከላው ውስጥ አይካተትም።
ትርጉሞችን ይመልከቱ
ቋንቋ: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ስፔንኛ ተጨማሪ (67)