+ -

عَن أَبِي سَعِيدٍ الْخُدْرِيِّ رضي الله عنه أَنَّ رَسُولَ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ قَالَ:
«لَا يَنْظُرُ الرَّجُلُ إِلَى عَوْرَةِ الرَّجُلِ، وَلَا الْمَرْأَةُ إِلَى عَوْرَةِ الْمَرْأَةِ، وَلَا يُفْضِي الرَّجُلُ إِلَى الرَّجُلِ فِي ثَوْبٍ وَاحِدٍ، وَلَا تُفْضِي الْمَرْأَةُ إِلَى الْمَرْأَةِ فِي الثَّوْبِ الْوَاحِدِ».

[صحيح] - [رواه مسلم] - [صحيح مسلم: 338]
المزيــد ...

ከአቡ ሰዒድ አልኹድሪይ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል:
"ወንድ ልጅ ወደ ወንድ ልጅ ሀፍረተ ገላ አይመልከት! ሴት ልጅም ወደ ሴት ልጅ ሀፍረተ ገላ አትመልከት! ወንድ ልጅ ከሌላ ወንድ ጋር በአንድ ልብስ ውስጥ አይጠቅለል! ሴት ልጅም ከሌላ ሴት ጋር በአንድ ልብስ ውስጥ አትጠቅለል!"

[ሶሒሕ ነው።] - [ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 338]

ትንታኔ

ነቢዩ ( የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ወንድ ልጅ ወደ ሌላ ወንድ ልጅ ሀፍረተ ገላ መመልከቱን ወይም ሴት ልጅ ወደ ሌላ ሴት ልጅ ሀፍረተ ገላ መመልከቷን ከለከሉ።
ሀፍረተ ገላ ማለት: ግልፅ የሆነ ጊዜ የሚያሳፍር የሆነ አካል ሁሉ ነው። የወንድ ልጅ ሀፍረተ ገላ ከእምብርት እስከ ጉልበቱ ሲሆን፤ የሴት ልጅ ደግሞ ከባዕድ ወንዶች አንፃር ሁሉም ሰውነቷ ሀፍረተ ገላ ነው። ከሴቶችና ከዘመዶቿ አንፃር ደግሞ በተለምዶ ቤት ውስጥ ስሰራ ግልፅ የሚሆነውን ያክል ግልፅ ታደርጋለች።
ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ወንድ ልጅ ተራቁቶ ከሌላው ወንድ ጋር በአንድ ልብስ ውስጥ ወይም ለብቻቸው ከአንድ ብርድ ልብስ ስር መገለላቸውን ከለከሉ። ሴት ልጅም ተራቁታ ወደ ሴት ልጅ በአንድ ልብስ ውስጥ ወይም ለብቻቸው ከአንድ ብርድ ልብስ ስር መገለላቸውን ከለከሉ። ምክንያቱም ይህ አንዱ የሌላኛው ጓደኛውን ሀፍረተ ገላ ወደመንካት ያደርሰዋልና። መንካቱ ደግሞ እንደማየቱ ክልክል ነው። እንደውም ወደ ትልቅ ብክለት ስለሚያመራ መንካቱ ከማየትም በበለጠ ክልክል ነው።

ትርጉም: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ስፔንኛ ኢንዶኔዥያኛ ኡይጙራዊ ባንጋሊኛ ፈረንሳይኛ ቱርክኛ ሩስያኛ ቦስንያኛ ሲንሃላዊ ህንድኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ቬትናማዊ ታጋሎግ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ማላያላምኛ ቴልጉ ስዋሒልኛ ታይላንድኛ ቡሽትኛ አሳምኛ السويدية الهولندية الغوجاراتية Kyrgyzisht النيبالية Jorubisht الليتوانية الدرية الصربية الصومالية Kinjaruandisht الرومانية المجرية التشيكية Malagasisht Oromisht Kannadisht الولوف الجورجية
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. ባልና ሚስት ካልሆኑ በቀር ሀፍረተ ገላን ከመመልከት መከልከሉን እንረዳለን።
  2. ኢስላም ማህበረሰቡን በማፅዳትና ለብልሹነት የሚያደርሱ መንገዶችን በመዝጋት ላይ ያለውን ጥረት እንረዳለን።
  3. እንደ ህክምና ለመሰሉ ጉዳዮች ሀፍረተ ገላን መመልከት አስፈላጊ ሆኖ የተገኘ ጊዜ መመልከት ይፈቀዳል። ነገር ግን ከስሜት ውጪ በሆነ ሁኔታ መሆን ይገባዋል።
  4. ሙስሊም ሀፍረተ ገላውን በመሸፈን ላይና የሌላን ሰው ሀፍረተ ገላ ከመመልከት አይኑን ዝቅ በማድረግ ላይ መታዘዙን እንረዳለን።
  5. ክልከላው ወንዶችን ከወንዶች ጋር፣ ሴቶችን ከሴቶች ጋር ብቻ በመከልከል መገደቡ ማየትና ሀፍረተ ገላን መግለጥ ብዙ ጊዜ ቀለል ተደርጎ የሚታይ ስለሆነ ነው።