عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُ قَالَ: قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ:
«مَنْ حَلَفَ فَقَالَ فِي حَلِفِهِ: وَاللَّاتِ وَالعُزَّى، فَلْيَقُلْ: لاَ إِلَهَ إِلَّا اللَّهُ، وَمَنْ قَالَ لِصَاحِبِهِ: تَعَالَ أُقَامِرْكَ، فَلْيَتَصَدَّقْ».
[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح البخاري: 4860]
المزيــد ...
ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ብለዋል:
"የማለ ሰው በመሀላውም 'በላትና ዑዛ እምላለሁ' ያለ ሰው 'ላኢላሃ ኢለሏህ' ይበል። ለባልደረባው 'ና ቁማር እንጫወት' ያለ ሰውም ይመፅውት።"
[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ አልቡኻሪ - 4860]
ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ከአላህ ውጪ ከመማል አስጠነቀቁ። አማኝ የሆነ ሰው ከአላህ በቀር በማንም አይምልምና። ከአላህ ውጪ የማለና ለምሳሌ በላት፣ በዑዛ የማለ ሰው (እነዚህ ሁለቱ ከእስልምና በፊት በድንቁርና ዘመን ይመለኩ የነበሩ ጣዖታት ናቸው።) ነፍሱን ለማዳን ከሽርክ ለመፅዳትና ለዛ መሀላው ማካካሻ እንዲሆነው አስከትሎ "ላኢላሃ ኢለሏህ" የማለት ግዴታ እንዳለበት ተናገሩ።
ቀጥለውም ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ለባልደረባው "ና ቁማር እንጫወት" ያለ ሰው (ቁማር ማለት ሁለት ወይም ከዛ በላይ የሆኑ ሰዎች በመካከላቸው አሸናፊው የሚወስደው ገንዘብ መድበው ለመሸናነፍ መጫወት ነው። ከመካከላቸውም እያንዳንዳቸው ወይ ያተርፋል ወይ ይከፍላል።) የጠራበትን ወንጀል ለማካካስ አንዳች ነገር መመፅወቱ እንደሚወደድለት ተናገሩ።