عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ رضي الله عنه قَالَ: قَالَ رَسُولُ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ:
«أَيُحِبُّ أَحَدُكُمْ إِذَا رَجَعَ إِلَى أَهْلِهِ أَنْ يَجِدَ فِيهِ ثَلَاثَ خَلِفَاتٍ عِظَامٍ سِمَانٍ؟» قُلْنَا: نَعَمْ. قَالَ: «فَثَلَاثُ آيَاتٍ يَقْرَأُ بِهِنَّ أَحَدُكُمْ فِي صَلَاتِهِ خَيْرٌ لَهُ مِنْ ثَلَاثِ خَلِفَاتٍ عِظَامٍ سِمَانٍ».
[صحيح] - [رواه مسلم] - [صحيح مسلم: 802]
المزيــد ...
አቡ ሁረይራ -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና- እንዲህ አሉ፦ የአላህ መልክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን እንዲህ አሉ፦
"አንዳችሁ ወደ ቤተሰቡ የተመለሰ ጊዜ ሶስት ትላልቅ የሰቡ እርጉዝ ግመሎችን ቢያገኝ ያስደስተዋልን?" እኛም "አዎን" አልን። እሳቸውም "አንዳችሁ በሰላቱ ውስጥ የሚያነባቸው ሶስት አንቀፆች ከሶስት ትላልቅ የሰቡ እርጉዝ ግመሎች ለሱ የተሻሉ ናቸው።" አሉ።
[ሶሒሕ ነው።] - [ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 802]
ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን ሰላት ውስጥ ሶስት አንቀፆችን በማንበብ የሚገኘው ምንዳ አንድ ሰው ቤቱ ውስጥ ሶስት የሰቡ ትላልቅ እርጉዝ ግመሎችን ከሚያገኝ እንደሚበልጥ ገለፁ።