عن سَمُرَة بن جندبٍ رضي الله عنه قال: قال رسول الله صلى الله عليه وسلم:
«أَحَبُّ الْكَلَامِ إِلَى اللهِ أَرْبَعٌ: سُبْحَانَ اللهِ، وَالْحَمْدُ لِلهِ، وَلَا إِلَهَ إِلَّا اللهُ، وَاللهُ أَكْبَرُ، لَا يَضُرُّكَ بِأَيِّهِنَّ بَدَأْتَ».

[صحيح] - [رواه مسلم]
المزيــد ...

ከሰሙረህ ቢን ጁንዱብ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: የአላህ መልክተኛ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ አሉ:
"አላህ ዘንድ ተወዳጅ የሆኑ ንግግሮች አራት ናቸው። 'ሱብሓነላህ' (አላህ ሆይ! ጥራት ተገባህ) 'አልሐምዱ ሊላህ' (ምስጋና ለአላህ የተገባ ነው።) 'ላኢላሃ ኢለላህ' (ከአላህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ የለም) 'አሏሁ አክበር' (አላህ ታላቅ ነው።) በማንኛቸውም ብትጀምር አይጎዳህም።"

Sahih/Authentic. - [Muslim]

ትንታኔ

ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም አላህ ዘንድ ተወዳጅ ንግግሮች አራት መሆናቸውን ተናገሩ:
"ሱብሓነላህ": ማለትም አላህን ከሁሉም ጉድለት ማጥራት ነው።
"አልሐምዱ ሊላህ": አላህን ከመውደድና ከማላቅ ጋር በምሉዕነት ባህሪ መግለፅ ነው።
"ላኢላሃ ኢለላህ": ማለትም ከአላህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ የለም።
"አላሁ አክበር": ማለትም አላህ ከሁሉም ነገር የበለጠ ታላቅና ሀያል ነው።
ትሩፋቷንና ምንዳዋን ለማግኘት የቃላቱን ቅደም ተከተል መጠበቅ ግዴታ አይደለም።

ትርጉም: እንግሊዝኛ ፈረንሳይኛ ስፔንኛ ቱርክኛ የኡርዱ ቋንቋ ኢንዶኔዥያኛ ቦስንያኛ ሩስያኛ ባንጋሊኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ታጋሎግ ህንድኛ ቬትናማዊ ሲንሃላዊ ኡይጙራዊ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ማላያላምኛ ቴልጉ ስዋሒልኛ ታሚልኛ ቦርምኛ ታይላንድኛ ጀርመንኛ ጃፓንኛ ቡሽትኛ አሳምኛ አልባንኛ السويدية الهولندية الغوجاراتية الدرية
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. በማንኛውም ቃል መጀመር ምንም ችግር አለማሳደሩ ሸሪዓ ገር መሆኑን ያስረዳናል።