+ -

عَنْ أَبِي سَعِيدٍ الْخُدْرِيِّ وَأَبِي هُرَيْرَةَ رضي الله عنهما عَنِ النَّبِيِّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ قَالَ:
«يُنَادِي مُنَادٍ: إِنَّ لَكُمْ أَنْ تَصِحُّوا فَلَا تَسْقَمُوا أَبَدًا، وَإِنَّ لَكُمْ أَنْ تَحْيَوْا فَلَا تَمُوتُوا أَبَدًا، وَإِنَّ لَكُمْ أَنْ تَشِبُّوا فَلَا تَهْرَمُوا أَبَدًا، وَإِنَّ لَكُمْ أَنْ تَنْعَمُوا فَلَا تَبْأَسُوا أَبَدًا» فَذَلِكَ قَوْلُهُ عَزَّ وَجَلَّ: {وَنُودُوا أَنْ تِلْكُمُ الْجَنَّةُ أُورِثْتُمُوهَا بِمَا كُنْتُمْ تَعْمَلُونَ} [الأعراف: 43].

[صحيح] - [رواه مسلم] - [صحيح مسلم: 2837]
المزيــد ...

ከአቡ ሰዒድ አልኹድሪይና ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ብለዋል:
«(ለጀነት ነዋሪዎች) አንድ ተጣሪ ይጣራና "ለናንተ ጤና አላችሁ መቼም አትታመሙም፤ ለናንተ ህይወት አላችሁ መቼም አትሞቱም፤ ለናንተ ወጣትነት አላችሁ መቼም አታረጁም፤ ለናንተ በፀጋ ውስጥ መጣቀም አላችሁ መቼም አትቸገሩም።" ይህም ይህ የአላህ ዐዘ ወጀል ንግግር ነው: {ይህች ጀነት ትሰሩት በነበራችሁት ተሰጣችኋት በማለት ይጠራሉ።} [አልአዕራፍ: 43]»

[ሶሒሕ ነው።] - [ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 2837]

ትንታኔ

ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና የጀነት ነዋሪዎች በጀነት ውስጥ እየተጣቀሙ ሳሉ አንድ ተጣሪ እንዲህ በማለት እንደሚጣራ አወሱ "ጀነት ውስጥ ለናንተ ጤና አላችሁ መቼም ትንሽ እንኳ ብትሆን ህመም አትታመሙም። ለናንተ ህያውነት አላችሁ፤ ትንሿ ሞት የሆነችውን እንቅልፍ እንኳ ቢሆን መቼም ጀነት ውስጥ አትሞቱም። ለናንተ ወጣትነት አላችሁ፤ መቼም ጀነት ውስጥ አታረጁም። ለናንተ ጀነት ውስጥ መጣቀም አላችሁ፤ መቼም ጀነት ውስጥ አታዝኑምም አትቸገሩምም። ይህም ይህ የአላህ ዐዘ ወጀል ንግግር ነው: {ይህች ጀነት ትሰሩት በነበራችሁት ተሰጣችኋት በማለት ይጠራሉ።} [አልአዕራፍ: 43]

ትርጉም: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ስፔንኛ ኢንዶኔዥያኛ ኡይጙራዊ ባንጋሊኛ ፈረንሳይኛ ቱርክኛ ሩስያኛ ቦስንያኛ ሲንሃላዊ ህንድኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ቬትናማዊ ታጋሎግ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ማላያላምኛ ስዋሒልኛ ታይላንድኛ ጀርመንኛ ቡሽትኛ አሳምኛ الهولندية الغوجاراتية الرومانية
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. ሰውዬው ምንም ያህል መጣቀም ላይ ቢደርስ እንኳ የዱንያን ህይወት ፀጋ ከሚያጣብቡ ነገሮች መካከል ትልልቆቹ አራት ነገሮች ናቸው: በሽታ፣ ሞት፣ እርጅናና ጠላትን፣ ድህነትን፣ ጦርነትንና ከዚህም ውጪ ባሉ ስጋቶች የሚያጋጥሙ ችግርና ሀዘን ናቸው። የጀነት ነዋሪዎች ከነዚህ የፀዱ ናቸው። የጀነት ነዋሪዎች የሚያገኙት የተሟላውን ፀጋ ነው።
  2. የጀነት ፀጋ ዱንያ ውስጥ ካለው ፀጋ እንደሚለያይ እንረዳለን። ይህም የጀነት ፀጋ ፍርሃት የሌለበት ስለሆነና የዱንያ ፀጋ ደግሞ የማይዘወትርና በሽታና ህመም የሚጋረጥበት ስለሆነ ነው።
  3. ወደ ጀነት ፀጋ የሚዳረሱበትን መልካም ስራ በመስራት ላይ መነሳሳቱን እንረዳለን።