عَنْ أَنَسِ بْنِ مَالِكٍ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُ عَنِ النَّبِيِّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ قَالَ:
«يَقُولُ اللَّهُ تَعَالَى لِأَهْوَنِ أَهْلِ النَّارِ عَذَابًا يَوْمَ القِيَامَةِ: لَوْ أَنَّ لَكَ مَا فِي الأَرْضِ مِنْ شَيْءٍ أَكُنْتَ تَفْتَدِي بِهِ؟ فَيَقُولُ: نَعَمْ، فَيَقُولُ: أَرَدْتُ مِنْكَ أَهْوَنَ مِنْ هَذَا، وَأَنْتَ فِي صُلْبِ آدَمَ: أَلّاَ تُشْرِكَ بِي شَيْئًا، فَأَبَيْتَ إِلَّا أَنْ تُشْرِكَ بِي».
[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح البخاري: 6557]
المزيــد ...
ከአነስ ቢን ማሊክ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል፦
«የትንሳኤ ቀን ከእሳት ነዋሪዎች እጅግ ዝቅተኛ ቅጣት ለሚቀጣው አላህ እንዲህ ይለዋል: "ምድር ውስጥ የሚገኙ ነገሮች ሁሉ ቢኖርህ ያንን ነገር ፍዳ ታደርገዋለህን?" እርሱም: "አዎን" ይላል። አላህም "በአደም ጀርባ እያለህ ካንተ ከዚህም ያነሰ ነገር ነበር የፈለግኩት: በኔ አንዳችንም አታጋራ ነበር ያልኩህ። አንተ ግን በኔ ማጋራትን እንጂ ሌላውን ነገር እምቢ አልክ።"»
[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ አልቡኻሪ - 6557]
ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ከእሳት ነዋሪዎች መካከል እሳት ከገባ በኋላ ዝቅተኛውን ቅጣት ለሚቀጣው አላህ እንዲህ እንደሚለው ተናገሩ: ላንተ ዱንያና በውስጧ ያሉ ነገሮች ሁሉ ቢኖሩህ ከዚህ ቅጣት ፋንታ እነርሱን ፍዳ አታደርጋቸውምን? እርሱም: አዎን ይላል። አላህም እንዲህ ይለዋል: በአደም ጀርባ ሳለህ እኔ ካንተ ጋር ቃልኪዳን ስወስድ የፈለግኩትና ያዘዝኩህ ከዚህም የቀለለውን ነገር ነበር። እርሱም በኔ አንዳችንም አታጋራ የሚል ነበር። አንተ ግን ወደ ዱንያ ያመጣሁህ ጊዜ ማጋራትን እንጂ እምቢ አልክ።