+ -

عَنْ أَبِي سَعِيدٍ الخُدْرِيَّ رَضيَ اللهُ عنهُ قَالَ:
بَعَثَ عَلِيُّ بْنُ أَبِي طَالِبٍ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُ إِلَى رَسُولِ اللَّهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ مِنَ اليَمَنِ بِذُهَيْبَةٍ فِي أَدِيمٍ مَقْرُوظٍ، لَمْ تُحَصَّلْ مِنْ تُرَابِهَا، قَالَ: فَقَسَمَهَا بَيْنَ أَرْبَعَةِ نَفَرٍ، بَيْنَ عُيَيْنَةَ بْنِ بَدْرٍ وَأَقْرَعَ بْنِ حابِسٍ وَزَيْدِ الخَيْلِ، وَالرَّابِعُ: إِمَّا عَلْقَمَةُ وَإِمَّا عَامِرُ بْنُ الطُّفَيْلِ، فَقَالَ رَجُلٌ مِنْ أَصْحَابِهِ: كُنَّا نَحْنُ أَحَقَّ بِهَذَا مِنْ هَؤُلاَءِ، قَالَ: فَبَلَغَ ذَلِكَ النَّبِيَّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ فَقَالَ: «أَلاَ تَأْمَنُونِي وَأَنَا أَمِينُ مَنْ فِي السَّمَاءِ، يَأْتِينِي خَبَرُ السَّمَاءِ صَبَاحًا وَمَسَاءً»، قَالَ: فَقَامَ رَجُلٌ غَائِرُ العَيْنَيْنِ، مُشْرِفُ الوَجْنَتَيْنِ، نَاشِزُ الجَبْهَةِ، كَثُّ اللِّحْيَةِ، مَحْلُوقُ الرَّأْسِ، مُشَمَّرُ الإِزَارِ، فَقَالَ يَا رَسُولَ اللَّهِ اتَّقِ اللَّهَ، قَالَ: «وَيْلَكَ، أَوَلَسْتُ أَحَقَّ أَهْلِ الأَرْضِ أَنْ يَتَّقِيَ اللَّهَ» قَالَ: ثُمَّ وَلَّى الرَّجُلُ، قَالَ خَالِدُ بْنُ الوَلِيدِ: يَا رَسُولَ اللَّهِ، أَلاَ أَضْرِبُ عُنُقَهُ؟ قَالَ: «لاَ، لَعَلَّهُ أَنْ يَكُونَ يُصَلِّي» فَقَالَ خَالِدٌ: وَكَمْ مِنْ مُصَلٍّ يَقُولُ بِلِسَانِهِ مَا لَيْسَ فِي قَلْبِهِ، قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ: «إِنِّي لَمْ أُومَرْ أَنْ أَنْقُبَ عَنْ قُلُوبِ النَّاسِ وَلاَ أَشُقَّ بُطُونَهُمْ» قَالَ: ثُمَّ نَظَرَ إِلَيْهِ وَهُوَ مُقَفٍّ، فَقَالَ: «إِنَّهُ يَخْرُجُ مِنْ ضِئْضِئِ هَذَا قَوْمٌ يَتْلُونَ كِتَابَ اللَّهِ رَطْبًا، لاَ يُجَاوِزُ حَنَاجِرَهُمْ، يَمْرُقُونَ مِنَ الدِّينِ كَمَا يَمْرُقُ السَّهْمُ مِنَ الرَّمِيَّةِ»، وَأَظُنُّهُ قَالَ: «لَئِنْ أَدْرَكْتُهُمْ لَأَقْتُلَنَّهُمْ قَتْلَ ثَمُودَ».

[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح البخاري: 4351]
المزيــد ...

ከአቡ ሰዒድ አልኹድሪይ (ረዺየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ:
«ዐሊይ ቢን አቢ ጧሊብ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - ከየመን በቀረዝ ቅጠል ታሽቶ በተዘጋጀ ከረጢት ከማዕድኑ አፈር ያልጠራን የወርቅ ቁርጥራጭ ወደ አላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ላከ። እሳቸውም ለአራት ሰዎች አከፋፈሉት። እነርሱም ዑየይና ቢን በድር፣ አቅረዕ ቢን ሓቢስ፣ ዘይድ አልኸይሊና አራተኛው ወይ ዐልቀማ ነው ወይም ዓሚር ቢን ጡፈይል ነው። ከርሳቸው ባልደረባ መካከል የሆነ አንድ ሰውዬም: "ከነዚህ የበለጠ እኛ የተገባን ነበርን!" አለ። ይህ ወሬም ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ዘንድ ደረሰና እንዲህ አሉ: "እኔ በሰማይ ላለው (ለአላህ) ታማኝ ሆኜ፤ የሰማይ ወሬም ጠዋትና ማታ እየመጣልኝ አታምኑኝምን?!።" በዚህ ጊዜም አንድ አይኑ የጎደጎደ፤ ከአይኑ ስር ያሉት አጥንቶቹ ወጣ ያሉ፤ ከቅንድቡ በላይ ያለው ግንባሩም ወጣ ያለ፤ ፂሙ የበዛ፤ ጭንቅላቱ የተላጨ፤ ሽርጡን ከቁርጭምጭሚቱ በላይ ከፍ አድርጎ የታጠቀ ሰውዬ ቆመና: "የአላህ መልክተኛ ሆይ! አላህን ይፍሩ!" አላቸው። እርሳቸውም "ወዮልህ! ከምድር ነዋሪዎች ባጠቃላይ አላህን ለመፍራት የተገባሁ እኔ አይደለሁምን?" አሉ። ከዚያም ሰውዮው ዘወር አለ። ኻሊድ ቢን ወሊድም "የአላህ መልክተኛ ሆይ! አንገቱን ልቅላውን?" አላቸው። እርሳቸውም "በፍፁም! ምናልባት እርሱ ይሰግድ ይሆናል።" አሉ። ኻሊድም "ቀልቡ ውስጥ የሌለውን እምነት (ለይዩልኝ) በአፉ እየተናገረ የሚሰግድ ስንት ሰው አለ አይደል እንዴ?!" አላቸው። የአላህ መልክተኛም (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) "እኔ የሰዎችን ቀልብ እንድሰነጥቅ፤ ሆዳቸውንም ከፍቼ እንድመለከት አልታዘዝኩኝም።" አሉ። ከዚያም ወደዚህ ሰውዬ ጀርባውን ሰጥቶ እየተመለከቱት እንዲህ አሉ: "ከዚህ ሰውዬ ዘርና ባልደረቦች የሆኑ የአላህን መጽሐፍ ቀሏቸው የሚያነቡ፤ የሚቀሩት ግን ከጉሮሮዋቸው የማያልፍ፤ ቀስት ሲወረወር ከኢላማው እንደሚሾልከው ከእስልምና ሾልከው የሚወጡ ሰዎች ይመጣሉ።" እንዲህም ብለዋል ይመስለኛል: "እኔ ከደረስኩባቸው የሠሙድ ህዝቦችን አገዳደል እገድላቸዋለሁ።"»

[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ አልቡኻሪ - 4351]

ትንታኔ

ዐሊይ ቢን አቢ ጧሊብ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - በቀረድ ታሽቶ በተሰራ ከረጢት ከአፈሩ ያልፀዳ የወርቅ ቁርጥራጮችን ከየመን ወደ አላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ላከ። ነቢዩም (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ለአራት ሰዎች አከፋፈሉት። እነርሱም: ዑየይና ቢን በድር አልፈዛሪይ፣ አቅረዕ ቢን ሓቢስ አልሐንዞሊይ፣ ዘይድ አልኸይሊ አንነብሃሊይ፣ ዐልቀማ ቢን ዐላሠህ አልዓሚሪይ ናቸው። ከርሳቸው ባልደረባ የሆነ አንድ ሰውዬም እንዲህ አለ: "በዚህ ስጦታ ከነዚህ በበለጠ እኛ የተገባን ነን።" ይህም ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ዘንድ ደረሰና እንዲህ አሉ: "እኔ በሰማይ ላለው (አላህ) ታማኝ ሆኜ የሰማይ ወሬ ጠዋትና ማታ እየመጣልኝ አታምኑኝምን?!" አይኖቹ ገባ ገባ ያሉ፤ የጉንጩ የላይኛው አጥንት ወጣ ያሉ፤ ግንባሩም ወጣ ያለ፤ ፂሙ ሳይረዝም የበዛ የሆነ፤ ጭንቅላቱን የተላጨ፤ የታችኛውን የሰውነት አካሉን የሚሸፍነው ሽርጡ ከፍ ያለ አንድ ሰውዬ ቆመና: "የአላህ መልክተኛ ሆይ! አላህን ይፍሩ!" አላቸው። እርሳቸውም (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) "ወዮልህ! ከምድር ነዋሪዎች ባጠቃላይ አላህን ለመፍራት የተገባሁ እኔ አይደለሁምን?" አሉት። ከዚያም ሰውዬው ዞሮ ሄደ። ኻሊድ ቢን ወሊድም: "የአላህ መልክተኛ ሆይ! አንገቱን አልቅላውምን?" አላቸው። እርሳቸውም "በፍፁም! ምናልባት የሚሰግድ ሊሆን ይችላል።" አሉት። ኻሊድም: "በቀልቡ የሌለውን በአፉ የሚናገር ስንት ሰጋጅ አለ?" አለ። እርሳቸውም (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን): "እኔ የሰዎችን ቀልብ እንድሰነጥቅም ሆነ ሆዳቸውን ቀድጄ እንድመለከት አልታዘዝኩም። እኔ የታዘዝኩት ሰዎችን በውጫዊ ማንነታቸው እንድይዛቸው ነው።" አሉ። ከዚያም ሰውዬው ጀርባውን ሰጥቶ መሄዱን ሳለ እየተመለከቱት እንዲህ አሉ: "ከዚህ ሰውዬ ዘር፣ ከባልደረቦቹ ወይም ከጎሳዎቹ መካከል የአላህን መጽሐፍ በጥሩ ድምፅ አሳምረው በመቅራት ምርጥ ችሎታው ያላቸው፤ አብዝተው ከመቅራታቸውም ምላሳቸው ርጥብ የሆኑ፤ ንባባቸው ግን ከጉሮሮዋቸው የማታልፍ። ከጉሮሮ አልፋ ቀልባቸው ጋር ደርሳ የምታስተካክላቸው ያልሆነች፤ ንባባቸውን አላህ ከፍ የማያደርጋትም የማይቀበላትም፤ ቀስት ከኢላማው በላይ ፈጥኖና በቀላሉ እንደሚወጣው ከእስልምና የሚወጡ ህዝቦች ይመጣሉ።" እንዲህም ብለዋል ይመስለኛል: "በሰይፋቸው በሙስሊሞች ላይ መውጣታቸውን ብደርስበት ኖሮ እንደ ሠሙድ ህዝቦች አገዳደል ከባድ አገዳደልን እገድላቸው ነበር።"

ትርጉም: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ስፔንኛ ኢንዶኔዥያኛ ኡይጙራዊ ባንጋሊኛ ፈረንሳይኛ ቱርክኛ ሩስያኛ ቦስንያኛ ሲንሃላዊ ህንድኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ቬትናማዊ ታጋሎግ ኩርዳዊ ሃውሳ ስዋሒልኛ ታይላንድኛ አሳምኛ الهولندية
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና በሚያውካቸው ነገር ላይ የነበራቸው ቻይነትና ትእግስትን እንረዳለን።
  2. የነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ነቢይነትን ማፅደቅና እርሳቸው የሚመጣላቸው ነገርም ከአላህ የሆነ ራዕይ መሆኑን እንረዳለን።
  3. ሰዎችን ከነርሱ ግልፅ በወጣው ላይ መኗኗር እንደሚገባንና የውስጣቸውንም አላህ እንዲቆጣጠረው መተው እንደሚገባን እንረዳለን።
  4. የሶላት ደረጃ የላቀ መሆኑን፤ ሶላት የሚሰግዱ ሰዎች በእስልምና ሐቅ ካልሆነ በቀር እንደማይገደሉ እንረዳለን።
  5. የኸዋሪጆችን አደገኛነት፤ እነርሱ የተዋጉ ጊዜ ጉዳታቸውን ለመከላከል እነርሱን መልሶ መዋጋት የተደነገገ እንደሆነ እንረዳለን።
  6. ነወዊይ እንዲህ ብለዋል: "እነርሱን በመዋጋት ላይ መነሳሳቱንና ዐሊይ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እነርሱን መዋጋቱ እርሱ ያለውን ደረጃ ያስረዳናል።"
  7. ቁርአንን ማስተንተን፤ መገንዘብ፤ በቁርአን መስራትና ቁርአንን አጥብቆ መያዝ ያለውን አንገብጋቢነት እንረዳለን።