+ -

عن عبد الله بن عمرو بن العاص رضي الله عنهما:
عن النبي صلى الله عليه وسلم أنه كان إذا دخل المسجد قال: «أعوذ بالله العظيم، وبوجهه الكريم، وسلطانه القديم، من الشيطان الرَّجِيم»، قال: أَقَطُّ؟ قلت: نعم، قال: فإذا قال ذلك قال الشيطان: حُفِظَ منِّي سائر اليوم.

[حسن] - [رواه أبو داود] - [سنن أبي داود: 466]
المزيــد ...

ከዐብደላህ ቢን ዐምር ቢን አልዐስ (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው:
ከነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንደተላለፈው: እርሳቸው መስጂድ በሚገቡ ወቅት እንዲህ ይሉ ነበር: "አዑዙ በላሂል ዐዚም ወቢወጅሂሂል ከሪም ወሱልጧኒሂል ቀዲም ሚነሽ-ሸይጧኒ ረጂም" "የሚሉት ይህን ብቻ ነውን? " ተብሎ ተጠየቀ። "አዎን" አልኩኝ። "ይህን ያለ ጊዜም ሸይጧን 'የቀረውን የቀኑን ክፍል ከኔ ተጠበቀ።' ይላል።" ትርጉሙም "ታላቅ በሆነው አላህ፣ በተከበረው ፊቱ፣ መጀመሪያም በሌለው ስልጣኑ ከተረገመው ሰይጣን እጠበቃለሁ።"

[ሐሰን ነው።] - [አቡዳውድ ዘግበውታል።] - [ሱነን አቡዳውድ - 466]

ትንታኔ

ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) መስጂድ በሚገቡ ወቅት እንዲህ ይሉ ነበር: (አዑዙ ቢላሂል ዐዚም) በአላህና በባህሪያቱ እከለላለሁ፣ እጠበቃለሁም። (ወቢወጅሂሂል ከሪም) ሰጪና ቸር በሆነው፤ (ወሱልጧኒሂ) ከፍጡራኖች መካከል በፈለገው ላይ ባለው አሸናፊነቱ፣ በችሎታውና በበላይነቱ (አልቀዲም) የመጀመሪያና ዘላለማዊ በሆነው፤ (ሚነሽ-ሸይጧኒ ረጂም) ከአላህ እዝነት የተባረረና የራቀ ከሆነው ሰይጣን እጠበቃለሁ። ማለትም: አላህ ሆይ! ከሰይጣን ጉትጎታ፣ ከማጥመሙ፣ ከእርምጃዎቹ፣ ውስጣችን ላይ ከሚፈጥረው ውልታና ማጥመም ጠብቀኝ ማለት ነው። ይህም የጥመት ምክንያትና ለመሀይምነትና መጥመም የሚያነሳሳው (ጠንሳሽ) እርሱ ስለሆነ ነው። ለዐብደላህ ቢን ዐምርም "ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ያሉት ይህን ብቻ ነውን?" ተብሎ ተጠየቀ። እርሱም "አዎን" አለ።
መስጂድ የሚገባ ሰው ይህን ዱዓ ካለም ሰይጣን እንዲህ ይላል: ይህ መስጂድ የገባው ሰው ነፍሱን በአጠቃላይ ወቅቱ ቀኑንም ምሽቱንም ከኔ ጠብቋታል።

ትርጉም: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ስፔንኛ ኢንዶኔዥያኛ ኡይጙራዊ ባንጋሊኛ ፈረንሳይኛ ቱርክኛ ሩስያኛ ቦስንያኛ ሲንሃላዊ ህንድኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ቬትናማዊ ታጋሎግ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ማላያላምኛ ቴልጉ ስዋሒልኛ ታይላንድኛ ቡሽትኛ አሳምኛ السويدية الهولندية الغوجاراتية Kyrgyzisht النيبالية الصربية الرومانية Malagasisht الجورجية
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. መስጂድ በሚገባ ወቅት በዚህ ዚክር ዱዓ የማድረግን ትሩፋት እንረዳለን። ይህ ዚክር ተናጋሪውን የተቀረውን ቀኑን ከሰይጣን ይጠብቀዋልና።
  2. ከሰይጣን መጠንቀቅ እንደሚገባ እንረዳለን። ሰይጣንም ሙስሊምን ለማጥመምና ለማሳሳት የሚጠባበቅ መሆኑን እነረዳለን።
  3. የሰው ልጅ በቀልቡ ባለው በአላህ የማመን፣ ይህን ዱዓ ማለትና ይህን ዱዓ ተከትሎ በተገባው ቃል (ምንዳ) እንደማመኑ ልክ ከሰይጣን ማጥመምና ማሳሳት ጥበቃን ያገኛል።
ተጨማሪ