+ -

عَنْ أَبِي سَعِيدٍ الخُدْرِيِّ رضي الله عنه قَالَ: قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ:
«إِنَّ اللَّهَ تَبَارَكَ وَتَعَالَى يَقُولُ لِأَهْلِ الجَنَّةِ: يَا أَهْلَ الجَنَّةِ؟ فَيَقُولُونَ: لَبَّيْكَ رَبَّنَا وَسَعْدَيْكَ، فَيَقُولُ: هَلْ رَضِيتُمْ؟ فَيَقُولُونَ: وَمَا لَنَا لاَ نَرْضَى وَقَدْ أَعْطَيْتَنَا مَا لَمْ تُعْطِ أَحَدًا مِنْ خَلْقِكَ؟ فَيَقُولُ: أَنَا أُعْطِيكُمْ أَفْضَلَ مِنْ ذَلِكَ، قَالُوا: يَا رَبِّ، وَأَيُّ شَيْءٍ أَفْضَلُ مِنْ ذَلِكَ؟ فَيَقُولُ: أُحِلُّ عَلَيْكُمْ رِضْوَانِي، فَلاَ أَسْخَطُ عَلَيْكُمْ بَعْدَهُ أَبَدًا».

[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح البخاري: 6549]
المزيــد ...

ከአቡ ሰዒድ አልኹድሪይ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ፦ «የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል፦
"አላህ ተባረከ ወተዓላ ለጀነት ነዋሪዎች እንዲህ ይላቸዋል: 'እናንተ የጀነት ነዋሪዎች ሆይ!' እነርሱም 'ደጋግመን በደስተኝነት አቤት ብለናል' ይላሉ። አላህም 'ተደሰታችሁን?' ይላቸዋል። እነርሱም 'ከፍጥረታቶችህ ለአንድም አካል ያልሰጠኸውን ሰጥተኸን እንዴት ነው የማንደሰተው?' ይላሉ። እርሱም 'እኔ ከዚህም የተሻለ ነገር እሰጣችኋለሁ።' ይላል። እነርሱም 'ጌታችን ሆይ! ከዚህ የተሻለ ምን አይነት ነገር ይኖራል?' ይላሉ። አላህም 'በናንተ ላይ ውዴታዬን አሰፍናለሁ። በናንተ ላይ ከዚህ በኋላ መቼም አልቆጣም።' ይላቸዋል።"»

[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ አልቡኻሪ - 6549]

ትንታኔ

ነቢዩ ((የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) አላህ ለጀነት ነዋሪዎች በውስጧ እያሉ እንዲህ እንደሚል ነገሩን: "የጀነት ነዋሪዎች ሆይ!" እነርሱም "ደጋግመን በደስተኝነት አቤት ብለናል" በማለት ለርሱ ይመልሳሉ። እርሱም ለነርሱ: ተደሰታችሁን? ይላቸዋል። እነርሱም: አዎን ተደስተናል። ከፍጥረታቶችህ ለአንድም አካል ያልሰጠኸውን ሰጥተኸን እንዴት ነው የማንደሰተው? ይላሉ። አላህም: ከዚህ የተሻለ ነገር ልስጣችሁን? ይላቸዋል። እነርሱም: ጌታችን ሆይ! ከዚህ የተሻለ ነገር ምን አለና? ይላሉ። እርሱም: ዘውታሪ የሆነውን ውዴታዬን አሰፍንባችኋለሁ። ከዚህ በኋላ በናንተ ላይ መቼም አልቆጣም። ይላቸዋል።

ትርጉም: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ስፔንኛ ኢንዶኔዥያኛ ባንጋሊኛ ፈረንሳይኛ ቱርክኛ ሩስያኛ ቦስንያኛ ሲንሃላዊ ህንድኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ቬትናማዊ ታጋሎግ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ማላያላምኛ ስዋሒልኛ ታይላንድኛ ቡሽትኛ አሳምኛ الهولندية الغوجاراتية Kyrgyzisht النيبالية الرومانية Malagasisht
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. አሸናፊና የበላይ የሆነው አላህ ከጀነት ነዋሪዎች ጋር እንደሚያወራ እንረዳለን።
  2. የጀነት ነዋሪዎች አላህ ከነርሱ እንደሚወድላቸው፤ በነርሱ ላይ ውዴታው እንደሚሰፍንና በነርሱ ላይ መቼም እንደማይቆጣ በአላህ መበሰራቸውን እንረዳለን።
  3. የጀነት ነዋሪዎች ስፍራቸው ከመለያየቱና ደረጃቸው ከመበላለጡም ጋር ሁሉም ባሉበት ሁኔታ ደስተኞች እንደሚሆኑ እንረዳለን። ምክንያቱም ሁሉም በአንድ ቃል የሚመልሱት "ከፍጥረታቶችህ ለአንድም አካል ያልሰጠኸውን ሰጥተኸናል።" በማለት ነውና።
ተጨማሪ