+ -

عَنْ ابْنَ عُمَرَ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُمَا قَالَ: سَمِعْتُ رَسُولَ اللَّهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ يَقُولُ:
«إِذَا رَأَيْتُمُوهُ فَصُومُوا، وَإِذَا رَأَيْتُمُوهُ فَأَفْطِرُوا، فَإِنْ غُمَّ عَلَيْكُمْ فَاقْدُرُوا لَهُ».

[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح البخاري: 1900]
المزيــد ...

ከኢብኑ ዑመር (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «የአላህን መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ሲሉ ሰምቻቸዋለሁ:
"ጨረቃን ባያችሁ ጊዜ ፁሙ! ባያችሁት ጊዜ ፆም ፍቱ! ከተጋረደባችሁ ደሞ ልኩን ገምቱለት።"»

[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ አልቡኻሪ - 1900]

ትንታኔ

ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና የረመዿን ወር መግቢያና መውጫን ምልክት ገለፁ። እንዲህ አሉ: የረመዿንን ጨረቃ ያያችሁ ጊዜ ፁሙ። በናንተና በጨረቃው መካከል ደመና ከገባና ከጋረዳችሁ ደሞ የሸዕባንን ወር ሰላሳ አድርጋችሁ ቁጠሩ። የሸዋልን ጨረቃ ያያችሁ ጊዜ ፆም ፍቱ። በናንተና በጨረቃው መካከል ደመና ከገባና ከጋረዳችሁ የረመዿንን ወር ሰላሳ አድርጋችሁ ቁጠሩ።

ትርጉም: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ስፔንኛ ኢንዶኔዥያኛ ኡይጙራዊ ባንጋሊኛ ፈረንሳይኛ ቱርክኛ ሩስያኛ ቦስንያኛ ሲንሃላዊ ህንድኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ቬትናማዊ ታጋሎግ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ማላያላምኛ ስዋሒልኛ ታይላንድኛ ቡሽትኛ አሳምኛ الهولندية الغوجاراتية الرومانية Oromisht
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. የወር መግባት ለማረጋገጥ የምንደገፈው በሂሳብ ሳይሆን ጨረቃን በማየት ነው።
  2. የረመዿን ወር መግባቱን ጨረቃን ሳያዩ በሂሳብ ላይ ብቻ በመመርኮዝ መጾም ግዴታ እንዳልሆነ ኢብኑል ሙንዚር የዑለሞችን ሙሉ ስምምነት ጠቅሰዋል።
  3. የረመዿንን ጨረቃ ከማየት ደመና ወይም መሰል ነገር ከጋረደ ሸዕባንን ሰላሳ ቀን መሙላት ግዴታ ነው።
  4. የጨረቃ ወር ሀያ ዘጠኝ ቀን ወይም ሰላሳ ቀን ብቻ ነው የሚሆነው።
  5. ደመና ወይም መሰል ነገር የሸዋልን ጨረቃ እንዳናይ ከጋረደ ረመዿንን ሰላሳ ቀን መሙላት ግዴታ ነው።
  6. በፆም ጉዳይ የሙስሊሞችን ሁኔታ የሚከታተል በሌለበት ስፍራ የሚኖር ወይም ይህንን ችላ በሚሉ ሰዎች ባሉበት ስፍራ የሚኖር ከሆነ ይህንን በራሱ ወይም በሚያምነው ሰው በማየት የሚያረጋግጥበትን ነገር መከታተልና መጠባበቅ ይገባል። በዛም ላይ በመመርኮዝ ይጾማልም ይፈታልም።
ተጨማሪ