عَنِ البَرَاءِ بْنِ عَازِبٍ رضي الله عنه أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ قَالَ:
«المُسْلِمُ إِذَا سُئِلَ فِي القَبْرِ: يَشْهَدُ أَنْ لاَ إِلَهَ إِلَّا اللَّهُ وَأَنَّ مُحَمَّدًا رَسُولُ اللَّهِ»، فَذَلِكَ قَوْلُهُ: {يُثَبِّتُ اللَّهُ الَّذِينَ آمَنُوا بِالقَوْلِ الثَّابِتِ فِي الحَيَاةِ الدُّنْيَا وَفِي الآخِرَةِ} [إبراهيم: 27].
[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح البخاري: 4699]
المزيــد ...
ከበራእ ቢን ዓዚብ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል:
"ሙስሊም ቀብር ውስጥ በተጠየቀ ጊዜ ከአላህ በቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ እንደሌለና ሙሐመድም የአላህ መልክተኛ መሆናቸውን ይመሰክራል።" ይህም አላህ እንዲህ እንዳለው ነው: {አላህ እነዚያን ያመኑትን በቅርቢቱም ህይወት በመጨረሻይቱም (በመቃብር) በተረጋገጠው ቃል ላይ ያረጋቸዋል።} [ኢብራሂም:27]
[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ አልቡኻሪ - 4699]
አማኝ ቀብር ውስጥ ይጠየቃል። ለዚህ ስራ የተወከሉ ሁለት መላእክት ይጠይቁታል። እነሱም በበርካታ ሐዲሦች ስማቸው እንደተጠቀሰው ነኪርና ሙንከር ናቸው። ከአላህ በቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ እንደሌለና ሙሐመድም የአላህ መልክተኛ መሆናቸውን ይመሰክራል። ነቢዩም (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ይህ ነው አላህ የተረጋገጠው ቃል ብሎ የተናገረበት አሉ: {አላህ እነዚያን ያመኑትን በቅርቢቱም ህይወት በመጨረሻይቱም (በመቃብር) በተረጋገጠው ቃል ላይ ያረጋቸዋል።} [ኢብራሂም:27]