+ -

عَنْ عَبْدِ اللَّهِ بنِ مَسْعُودٍ رضي الله عنه أَنَّ النَّبِيَّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ قَالَ:
«سِبَابُ المُسْلِمِ فُسُوقٌ، وَقِتَالُهُ كُفْرٌ».

[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح البخاري: 48]
المزيــد ...

ከዐብደላህ ቢን መስዑድ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ብለዋል:
"ሙስሊምን መስደብ አመፀኝነት ነው። መግደሉ ክህደት ነው።"

[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ አልቡኻሪ - 48]

ትንታኔ

ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ሙስሊም የሆነ ሰው ሙስሊም ወንድሙን ከመሳደብና ከመዝለፍ ከለከሉ። ይህም አመፀኝነት ነው። ማለትም ከአላህ እና ከመልክተኛው ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ትእዛዝ መውጣት ነው። ሙስሊም የሆነ ሰው ሙስሊም ወንድሙን መጋደሉ ደግሞ የክህደት ስራ ነው። ነገር ግን ትንሹ ክህደት ነው።

ትርጉም: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ስፔንኛ ኢንዶኔዥያኛ ባንጋሊኛ ፈረንሳይኛ ቱርክኛ ሩስያኛ ቦስንያኛ ሲንሃላዊ ህንድኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ቬትናማዊ ታጋሎግ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ማላያላምኛ ስዋሒልኛ ታይላንድኛ ጀርመንኛ ቡሽትኛ አሳምኛ الهولندية الغوجاراتية النيبالية الرومانية Oromisht
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. የሙስሊምን ክብርና ደም ማክበር ግዴታ ነው።
  2. ያለአግባብ ሙስሊምን የሚሳደብ ሰው መጨረሻው ከባድ እንደሆነ ተገልጿል። ያለአግባብ የሚሳደብ ሰው አመፀኛ ነውና።
  3. ሙስሊምን መሳደብና መግደል ኢማንን ያደክመዋልም ያጎድለዋልም።
  4. አንዳንድ ስራዎች ከእስልምና መንገድ ወደሚያስወጣው ትልቁ ክህደት ባይደርሱም ክህደት ተብለው እንደሚጠሩ እንረዳለን።
  5. እዚህ ሐዲሥ ውስጥ ክህደት በማለት የሚፈለገው በአህሉ ሱናዎች ባጠቃላይ ስምምነት መሰረት ከእስልምና የማያስወጣውን ትንሹን ክህደት ነው። ምክንያቱም አላህ አማኞች በሚጋደሉበትና በሚጋጩበት ወቅት እንኳ ለነርሱ የእምነት ወንድማማችነትን አፅድቋልና። አላህ እንዲህ ብሏል {ከምእመናንም የሆኑ ሁለት ጭፍሮች ቢጋደሉ በመካከላቸው አስታርቁ} ከሚለው {ምእመናኖች ወንድማማቾች ናቸው።} [አል‐ሑጁራት: 9 ‐10] እስከሚለው ድረስ ይህን ያስረዳናል።