+ -

عَنْ ابْنِ عَبَّاسٍ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُمَا أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ قَالَ:
«إنَّ اللَّهَ تَجَاوَزَ لِي عَنْ أُمَّتِي الخَطَأَ وَالنِّسْيَانَ وَمَا اسْتُكْرِهُوا عَلَيْهِ».

[قال النووي: حديث حسن] - [رواه ابن ماجه والبيهقي وغيرهما] - [الأربعون النووية: 39]
المزيــد ...

ከኢብኑ ዓባስ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው «የአላህ መልክተኛ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - እንዲህ ብለዋል:
"አላህ ለኔ ከኡመቴ ላይ በመሳሳት፣ በመርሳትና በመገደድ ለሚያደርጉት ነገር ይቅር ብሏቸዋል።"»

[قال النووي: حديث حسن] - [رواه ابن ماجه والبيهقي وغيرهما] - [الأربعون النووية - 39]

ትንታኔ

ነቢዩ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- አላህ ለኡመታቸው በሶስት ሁኔታዎች ላይ እያሉ የሰሩትን ወንጀል ይቅር እንዳለ ተናገሩ:- የመጀመሪያው: በስህተት: ማለትም ሆነ ብለው ሳይሆን የሰሩት ወንጀል ማለት ነው። ይህም ማለት አንድ ሙስሊም በድርጊቱ አንዳችን ነገር ማሰቡና ድርጊቱ ግን ካሰበው ውጪ ሆኖ መገኘቱ ነው። ሁለተኛው: በመርሳት: ይህም ማለት አንድ ሙስሊም አንድን ነገር ለመስራት ያስባል። ነገር ግን ድርጊቱን ለመስራት ባሰበበት ወቅት ይረሳዋል። በዚህም ወንጀል አይኖርበትም። ሶስተኛው: በመገደድ ነው። አንድ ባሪያ መስራት ሳይፈልግና አስገዳጁንም አካል መከላከል በማይችልበት ሁኔታ ላይ ሆኖ ተገዶ አንድን ድርጊት ሊሰራ ይችላል። በዚህ ጊዜ በርሱ ላይ ወንጀል ወይም ጣጣ አይኖርበትም። የሐዲሡ ሃሳብ ግን በባሪያና በጌታው መካከል የተከለከለን በመስራት ላይ መርሳትን የሚመለከት ነው። ትእዛዝን ረስቶ ቢተው ግን ትእዛዙ አይነሳለትም። እነዚህን ነገሮች ተከትሎ የተከሰተ ወሰን አላፊነት ካለ የፍጡርም ሐቅ አይነሳለትም። በስህተት የገደለ ሰው ለምሳሌ በርሱ ላይ ጉማ ይኖርበታል። ወይም በስህተት መኪና ቢያጠፋ በርሱ ላይ መኪናውን መክፈል አለበት።

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. የአላህ ዓዘ ወጀል እዝነት ስፋትና ለባሮቹ መራራቱን እንረዳለን። ይህም ባሮቹ ወንጀልን በነዚህ ሶስት ሁኔታዎች ላይ ሆነው ቢሰሩ ወንጀልነቱን ከነርሱ ላይ ማንሳቱ ነው።
  2. አላህ ለነቢዩ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- እና ለኡመታቸው የዋለውን ችሮታ ሰፊነቱን እንረዳለን።
  3. ወንጀልነቱ ይነሳል ማለት ብይኑ ወይም ካሳው ይነሳለታል ማለት አይደለም። ለምሳሌ ዉዱእን የረሳና ዉዱእ ያለው መስሎት የሰገደ ሰው በዚህ ወንጀል አይኖርበትም። ነገር ግን ዉዱእ ማድረግና ሶላቱን መድገም ይኖርበታል።
  4. በመገደድ ምክንያት ወንጀልነቱ እንዲነሳ የግድ መሟላት ያለባቸው መስፈርቶች አሉ።ለምሳሌ: አስገዳጁ የዛተውን ነገር በተገዳጁ ላይ ለመፈፀም አቅም ያለው መሆን አለበት።
ትርጉም: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ስፔንኛ ኢንዶኔዥያኛ ኡይጙራዊ ባንጋሊኛ ፈረንሳይኛ ቱርክኛ ሩስያኛ ቦስንያኛ ሲንሃላዊ ህንድኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ቬትናማዊ ታጋሎግ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ማላያላምኛ ቴልጉ ስዋሒልኛ ታሚልኛ ታይላንድኛ ጀርመንኛ ቡሽትኛ አሳምኛ አልባንኛ الغوجاراتية Kyrgyzisht النيبالية Jorubisht الليتوانية الدرية الصربية الطاجيكية Kinjaruandisht المجرية التشيكية الموري Kannadisht الولوف Azerisht الأوزبكية الأوكرانية الجورجية المقدونية الخميرية
ትርጉሞችን ይመልከቱ