عن أنس بن مالك رضي الله عنه:
أَنَّ النَّبِيَّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ كَانَ لَا يَرُدُّ الطِّيبَ.

[صحيح] - [رواه البخاري] - [صحيح البخاري: 2582]
المزيــد ...

ከአነስ ቢን ማሊክ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው
"ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ሽቶን አይመልሱም ነበር።"

[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪ ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ አልቡኻሪ - 2582]

ማብራሪያ

ከነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ቀናው ጎዳና መካከል ሽቶን መቀበልና አለመመለስ አንዱ ነበር። ምክንያቱም ለሸክም ቀላል መአዛው ምርጥ ነውና።

ከሐዲሡ የሚቀሰሙ ቁምነገሮች

  1. የሽቶን ስጦታ መቀበል ሸክሙ ምንም ጣጣ የማያመጣና ስለተቀበልነውም ምንም መመፃደቅን ስለማያመጣ ተወዳጅ ነው።
  2. ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ሽቶን ባለመመለሳቸውና ስጦታን ከሚሰጣቸው አካል በመቀበላቸው ውስጥ የሳቸውን የስነምግባር ማማርና ሙሉነት እንረዳለን።
  3. ሽቶን መጠቀም መበረታታቱን እንረዳለን።
ትርጉሞችን አሳይ
ቋንቋ: الإنجليزية الأوردية الإسبانية ተጨማሪ (64)