عَنِ ابْنِ عُمَرَ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُمَا أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ قَالَ:
«إِنَّمَا مَثَلُ صَاحِبِ القُرْآنِ كَمَثَلِ صَاحِبِ الإِبِلِ المُعَقَّلَةِ، إِنْ عَاهَدَ عَلَيْهَا أَمْسَكَهَا، وَإِنْ أَطْلَقَهَا ذَهَبَتْ».
[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح البخاري: 5031]
المزيــد ...
ከኢብኑ ዑመር ረዲየሏሁ ዐንሁማ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: የአላህ መልክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም - የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- እንዲህ ብለዋል:
"የቁርአን ባለቤት የሆነ ሰው ምሳሌ የታሰረ ግመል ባለቤት አምሳያ ነው። ከተቆጣጠራት (በአግባቡ) ይይዛታል። ከለቀቃት ግን ትሄዳለች።"
[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ አልቡኻሪ - 5031]
ነቢዩ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ቁርአንን የተማረ፣ በማንበብም ይሁን በቃል ሽምደዳ ማንበቡን ያዘወተረን ሰው ግመሉን ጉልበቷ ላይ በገመድ እንዳሰረ የግመል ባለቤት መሰሉት። ግመሏን በአግባቡ ከተቆጣጠረ እንደያዛት ይቀጥላል። ገመዱን ከፈታው ግን ግመሏ ትሄዳለችም ታመልጣለችም። የቁርአን ባለቤትም ካነበበው ያስታውሰዋል። ቁርአንን በአግባቡ ካልጠበቀ ግን ይረሳዋል። በአግባቡ ቁርአንን እስከተጠባበቀ ድረስም ሒፍዙም ከመኖር አይወገድም።