+ -

عَنِ ابْنِ عَبَّاسٍ رضي الله عنهما قَالَ:
«بَيْنَمَا جِبْرِيلُ قَاعِدٌ عِنْدَ النَّبِيِّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ سَمِعَ نَقِيضًا مِنْ فَوْقِهِ، فَرَفَعَ رَأْسَهُ، فَقَالَ: هَذَا بَابٌ مِنَ السَّمَاءِ فُتِحَ الْيَوْمَ لَمْ يُفْتَحْ قَطُّ إِلَّا الْيَوْمَ، فَنَزَلَ مِنْهُ مَلَكٌ، فَقَالَ: هَذَا مَلَكٌ نَزَلَ إِلَى الْأَرْضِ لَمْ يَنْزِلْ قَطُّ إِلَّا الْيَوْمَ، فَسَلَّمَ، وَقَالَ: أَبْشِرْ بِنُورَيْنِ أُوتِيتَهُمَا لَمْ يُؤْتَهُمَا نَبِيٌّ قَبْلَكَ: فَاتِحَةُ الْكِتَابِ، وَخَوَاتِيمُ سُورَةِ الْبَقَرَةِ، لَنْ تَقْرَأَ بِحَرْفٍ مِنْهُمَا إِلَّا أُعْطِيتَهُ».

[صحيح] - [رواه مسلم] - [صحيح مسلم: 806]
المزيــد ...

ከኢብኑ ዐባስ (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ:
«ጂብሪል ነቢዩ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - ዘንድ ተቀምጦ ሳለ ከበላዩ ድምፅ ሰማና ራሱን ቀና አደረገ። እንዲህም አለ: "ይህ ዛሬ የተከፈተ የሰማይ በር ነው። ከዛሬ በቀርም ተከፍቶ አያውቅም።" ከተከፈተው በርም መልአክ ወረደ። ጂብሪልም እንዲህ አለ: "ይህ ወደ ምድር የወረደ መልአክ ነው። ከዛሬ በቀርም በጭራሽ ወርዶ አያውቅም" መልአኩም ሰላምታን አቀረበና እንዲህ አለ: "ከአንተ በፊት ማንም ያልተሰጠው በሆነ ለአንተ ብቻ በተሰጠህ ሁለት ብርሃኖች አበስርሃለሁ። (እነርሱም) የመጽሐፉ መክፈቻ (ፋቲሓ) እና የበቀራ ምዕራፍ መጨረሻዎቹ ናቸው። ከነርሱም አንድም ፊደል አታነብም የሚሰጥህ ቢሆን እንጂ።"»

[ሶሒሕ ነው።] - [ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 806]

ትንታኔ

መልአኩ ጂብሪል ዐለይሂ ሰላም ነቢዩ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - ዘንድ ተቀምጦ ሳለ ከሰማይ በር ሲከፈት እንደሚያሰማው አይነት ድምፅ ሰማ። ጂብሪልም ራሱንና አይኑን ወደ ሰማይ ቀና አደረገ። ቀጥሎ ለነቢዩ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና -ይህ የሰማይ በር ዛሬ እንደተከፈተና ከዚህ ቀን በፊትም በፍፁም ተከፍቶ እንደማያውቅ ነገራቸው። ከሰማይም ወደ ምድር ከመልአኮች መካከል ከዛሬ በቀር ወርዶ የማያውቅ አንድ መልአክ ወረደ። መልአኩም ለነቢዩ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - ሰላምታን አቀረበና እንዲህ አላቸው: ከአንተ በፊት ለማንም ነቢይ ባልተሰጡና ለአንተ ብቻ በተሰጠህ ሁለቱ ብርሃኖች አበስርሃለሁ። እነርሱም: የፋቲሓ ምዕራፍና የበቀራ ምዕራፍ የመጨረሻዎቹ ሁለት አንቀጾች ናቸው። አስከትሎም መልአኩ እንዲህ አለ: አንድም ሰው ከነርሱ አንድ ፊደል እንኳ ብትሆን ካነበበ አላህ በውስጧ ያለውን መልካም ነገር፣ ተማፅኖና ፍላጎት ይሰጠዋል።

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. የፋቲሓ ምዕራፍና የበቀራ ምዕራፍ መጨረሻዎች ያላቸውን ደረጃና እነርሱን በመቅራትና ውስጣቸው ባለው መልዕክት በመስራት ላይ መነሳሳቱን እንረዳለን።
  2. ሰማይ መለኮታዊ ትእዛዛት የሚወርዱበት በሮች እንዳለውና የሰማይ በርም ያለ አላህ ትእዛዝ እንደማይከፈት እንረዳለን።
  3. ነቢዩ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - ጌታቸው ዘንድ ያላቸው ክብር ተገልጿል። ይኸውም ከርሳቸው በፊት ማንንም ነቢይ ባላከበረበት እርሳቸውን ማክበሩና እነዚህን ሁለት ብርሃኖች መስጠቱ ነው።
  4. ወደ አላህ ከመጣሪያ መንገዶች መካከል በመልካም ማበሰር አንዱ ነው።
ትርጉም: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ስፔንኛ ኢንዶኔዥያኛ ኡይጙራዊ ባንጋሊኛ ፈረንሳይኛ ቱርክኛ ሩስያኛ ቦስንያኛ ሲንሃላዊ ህንድኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ቬትናማዊ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ስዋሒልኛ ታይላንድኛ አሳምኛ الدرية الرومانية المجرية الجورجية الخميرية الماراثية
ትርጉሞችን ይመልከቱ
ተጨማሪ