عَنْ جَابِرِ بْنِ عَبْدِ اللهِ رضي الله عنهما أَنَّ رَسُولَ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ قَالَ:
«اتَّقُوا الظُّلْمَ، فَإِنَّ الظُّلْمَ ظُلُمَاتٌ يَوْمَ الْقِيَامَةِ، وَاتَّقُوا الشُّحَّ، فَإِنَّ الشُّحَّ أَهْلَكَ مَنْ كَانَ قَبْلَكُمْ، حَمَلَهُمْ عَلَى أَنْ سَفَكُوا دِمَاءَهُمْ وَاسْتَحَلُّوا مَحَارِمَهُمْ».
[صحيح] - [رواه مسلم] - [صحيح مسلم: 2578]
المزيــد ...
ከጃቢር ቢን ዐብደላህ (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል:
"በደልን ተጠንቀቁ! በደል የትንሳኤ ቀን ድርብርብ ጨለማዎች ነውና። ስስትንም ተጠንቀቁ! ስስት ከናንተ በፊት የነበሩትን ህዝቦች አጥፍቷልና። ስስታምነት ደማቸውን እንዲያፈሱና ሐራም (ያልተፈቀደውን) እንደ ሐላል አድርገው እንዲቆጥሩ አነሳስቷቸዋልና።"
[ሶሒሕ ነው።] - [ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 2578]
ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ከበደል አስጠነቀቁ። ከበደል መካከልም: ሰዎችን መበደል፣ ነፍስን መበደል፣ በአላህ ሐቅ ላይ በደል መፈፀም ይጠቀሳሉ። በደል ማለት ሁሉንም የሐቅ ባለቤቶችን ሐቃቸውን ከመስጠት መተው ነው። በደል የትንሳኤ ቀን በባለቤቱ ላይ ከሚያጋጥመው መከራዎችና አስፈሪ ክስተቶች አኳያ ጨለማ ነው። ከስስትም ከለከሉ። እርሱም ከመጓጓት (መንሰፍሰፍ) ጋር እጅግ ስስታምነት ነው። ከስስታምነት መካከል: ገንዘባዊ ሐቆችን ከመወጣት ቸል ማለትና ለዱንያ እጅግ መንገብገብን ይጠቀሳል። ይህኛው የበደል ክፍል ማለትም ስስታምነት ከእኛ በፊት የነበሩትን ህዝቦች አጥፍቷቸዋል። ይህም ከፊሉ ከፊሉን እንዲገድሉና አላህ እርም ያደረጋቸውን ክልክሎች የተፈቀዱ እንዲያደርጉ አነሳስቷቸዋል።