عَنْ عَبْدِ اللهِ بْنِ مَسْعُودٍ رضي الله عنه قَالَ: قَالَ رَسُولُ اللهِ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ:
«لَيْسَ الْمُؤْمِنُ بِالطَّعَّانِ وَلاَ اللَّعَّانِ وَلاَ الفَاحِشِ وَلاَ البَذِيءِ».
[صحيح] - [رواه الترمذي] - [سنن الترمذي: 1977]
المزيــد ...
ከዐብደላህ ቢን መስዑድ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድለላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ብለዋል:
"ሙእሚን የሆነ ሰው እጅግ ተቺ፣ እጅግ ተራጋሚ፣ ፀያፍ ተግባር ሰሪ፣ መጥፎ ንግግር ተናጋሪ አይደለም።"»
[ሶሒሕ ነው።] - [ቲርሚዚ ዘግበውታል።] - [ሱነን ቲርሚዚ - 1977]
ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ምሉዕ ኢማን ያለው አማኝ ሰዎችን በዘራቸው የሚተች፣ ስድብና እርግማን የሚያበዛ፣ ሃፍረተ ቢስነትን የተላበሰ ፀያፍ ድርጊትና ንግግርን የሚያበዛ እንዳልሆነ ተናገሩ።