عَنْ عَلِيٍّ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُ: إِذَا حَدَّثْتُكُمْ عَنْ رَسُولِ اللَّهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ فَلَأَنْ أَخِرَّ مِنَ السَّمَاءِ أَحَبُّ إِلَيَّ مِنْ أَنْ أَكْذِبَ عَلَيْهِ، وَإِذَا حَدَّثْتُكُمْ فِيمَا بَيْنِي وَبَيْنَكُمْ فَإِنَّ الحَرْبَ خَدْعَةٌ، سَمِعْتُ رَسُولَ اللَّهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ يَقُولُ:
«يَأْتِي فِي آخِرِ الزَّمَانِ قَوْمٌ حُدَثَاءُ الأَسْنَانِ سُفَهَاءُ الأَحْلاَمِ، يَقُولُونَ مِنْ خَيْرِ قَوْلِ البَرِيَّةِ، يَمْرُقُونَ مِنَ الإِسْلاَمِ كَمَا يَمْرُقُ السَّهْمُ مِنَ الرَّمِيَّةِ، لاَ يُجَاوِزُ إِيمَانُهُمْ حَنَاجِرَهُمْ، فَأَيْنَمَا لَقِيتُمُوهُمْ فَاقْتُلُوهُمْ، فَإِنَّ قَتْلَهُمْ أَجْرٌ لِمَنْ قَتَلَهُمْ يَوْمَ القِيَامَةِ».
[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح البخاري: 3611]
المزيــد ...
ከዐሊይ ረዲየሏሁ ዐንሁ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አለ: «ከአላህ መልክተኛ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- የነገርኳችሁ ጊዜ በርሳቸው ላይ ውሸትን ከምቀጥፍ ከሰማይ ብፈጠፈጥ እመርጣለሁ። በኔና በናንተ መካከል ባለ ጉዳይ ከነገርኳችሁ ግን ፍልሚያ ሽወዳ ነው። የአላህን መልክተኛ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- እንዲህ ሲሉ ሰምቻለሁ:
"በመጨረሻው ዘመን እድሜያቸው ለጋ፣ አስተሳሰባቸው የሞኝ የሆኑ ሰዎች ይመጣሉ። ከፍጡራን ንግግር የተሻለን ንግግርም ይናገራሉ። ቀስት (ኢላማውን) በስቶ እንደሚወጣው እነርሱም ከእስልምና ይወጣሉ። ኢማናቸው ከጉሮሯቸው አያልፍም። ባገኛችኋቸው ስፍራም ግደሏቸው። እነርሱን መግደልም ለገደላቸው ሰው የትንሳኤ ቀን ምንዳ ያስገኝለታል።"»
[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ አልቡኻሪ - 3611]
የአማኞች መሪ ዐሊይ ቢን አቢ ጧሊብ ረዺየሏሁ ዐንሁ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንዲህ ብሎ ተናገረ: "ከነቢዩ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- አንድን ንግግር ስናገር ከሰማችሁኝ እኔ አላሸሙርም በግልፅ ቋንቋ ነው የምነግራችሁ። በአላህ መልክተኛ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ላይ ውሸትን ከማወራ ከሰማይ ወድቄ ብፈጠፈጥ ይሻለኛል። በኔና በሰዎች መካከል ስላለ ጉዳይ ካወራሁ ፍልሚያ ሽወዳ ነውና አሸሙሬ ላወራ እችላለሁ። ነቢዩ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- እንዲህ ሲሉ ሰምቻለሁ: "በመጨረሻው ዘመን እድሜያቸው ለጋ የሆኑ ወጣቶች፣ አስተሳሰባቸው ደካማ የሆኑ ሰዎች ይመጣሉ። ከቁርአንም ይዘው ያወራሉ አብዝተውም ቁርአንን ያነባሉ። ቀስት ኢላማውን በስቶ እንደሚወጣው እነርሱም ከእስልምና ይወጣሉ። ድንበሩንም ይጥሳሉ። ኢማናቸው ከጉሮሯቸው አያልፍም። ባገኛችኋቸው ቦታም ግደሏቸው። እነርሱን መግደል ለገደላቸው ሰው የትንሳኤ ቀን ምንዳ ያሰጠዋል።"