عَنْ عَبْدِ اللهِ بنِ مَسْعُودٍ رَضيَ اللهُ عنهُ قَالَ: نَامَ رَسُولُ اللهِ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ عَلَى حَصِيرٍ، فَقَامَ وَقَدْ أَثَّرَ فِي جَنْبِهِ، فَقُلْنَا: يَا رَسُولَ اللهِ، لَوِ اتَّخَذْنَا لَكَ وِطَاءً، فَقَالَ:
«مَا لِي وَلِلدُّنْيَا، مَا أَنَا فِي الدُّنْيَا إِلاَّ كَرَاكِبٍ اسْتَظَلَّ تَحْتَ شَجَرَةٍ ثُمَّ رَاحَ وَتَرَكَهَا».
[صحيح] - [رواه الترمذي وابن ماجه] - [سنن الترمذي: 2377]
المزيــد ...
ከዐብደላህ ቢን መስዑድ ረዺየሏሁ ዐንሁ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «የአላህ መልክተኛ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ሰሌን ላይ ተኙ። ከተኙበት ሲነሱም ሰሌኑ ጎናቸው ላይ ሰንበር አውጥቷል። እኛም "የአላህ መልክተኛ ሆይ! ለርሶ ለስላሳ ፍራሽ ብናዘጋጅሎትስ?" አልን። እርሳቸውም:
"እኔና ዱንያ ምን አገናኘን? እኔ ዱንያ ውስጥ ዛፍ ስር ተጠልሎ ከዚያም ትቷት እንደሄደ ተጓዥ አምሳያ እንጂ ሌላ አይደለሁም።"»
[ሶሒሕ ነው።] - [ቲርሚዚና ኢብኑማጀህ ዘግበውታል።] - [ሱነን ቲርሚዚ - 2377]
ዐብደላህ ቢን መስዑድ ረዺየሏሁ ዐንሁ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንዳወሱት ነቢዩ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ከአንድ በዘንባባ ነገር ተሰፍቶ በተሰራ ትንሽ ምንጣፍ ላይ ተኙና ሲነሱም ሰሌኑ የጎናቸው ቆዳ ላይ ሰንበር አወጣ። እኛም እንዲህ አልን: "የአላህ መልክተኛ ሆይ! ለርሶ ለስላሳ ፍራሽ ብናዘጋጅሎት’ኮ በዚህ ሸካራ ሰሌን ላይ ከሚተኙ ይልቅ የተሻለ ይሆንሎታል።" ነቢዩም ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- እንዲህ አሉ: "ከዱንያ ጋር ወደርሷ እስክማረክ ድረስ የሚያደርሰኝ ውዴታ የለኝም። የኔና እርሷ ውስጥ ያለኝ ቆይታ ምሳሌ ዛፍ ስር ተጠልሎ ከዚያም ዛፏን ትቶ እንደሚሄድ ተጓዥ አምሳያ እንጂ ሌላ አይደለም።"