عَنْ عِمْرَانَ بْنِ حُصَيْنٍ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُمَا قَالَ: قَالَ النَّبِيُّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ:
«خَيْرُكُمْ قَرْنِي، ثُمَّ الَّذِينَ يَلُونَهُمْ، ثُمَّ الَّذِينَ يَلُونَهُمْ» قَالَ عِمْرَانُ: لاَ أَدْرِي أَذَكَرَ النَّبِيُّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ بَعْدُ قَرْنَيْنِ أَوْ ثَلاَثَةً، قَالَ النَّبِيُّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ: «إِنَّ بَعْدَكُمْ قَوْمًا يَخُونُونَ وَلاَ يُؤْتَمَنُونَ، وَيَشْهَدُونَ وَلاَ يُسْتَشْهَدُونَ، وَيَنْذِرُونَ وَلاَ يَفُونَ، وَيَظْهَرُ فِيهِمُ السِّمَنُ».
[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح البخاري: 2651]
المزيــد ...
ከዒምራን ቢን ሑሰይን (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ ብለዋል:
"ከናንተ ምርጡ እኔ ያለሁበት (ዘመን) ትውልድ ነው። ከዚያም ከነርሱ በኋላ ቀጥለው የሚመጡት፤ ከዚያም ከነርሱ ቀጥለው የሚመጡት ናቸው።" ዒምራንም እንዲህ አለ: "ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ከሳቸው ትውልድ በኋላ ሁለት ትውልዶችን ይጥቀሱ ወይም ሶስት አላውቅም።" ከዚያም ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ አሉ: "የሚከዱ የማይታመኑ፤ ምስክርነት ሳይጠየቁ የሚመሰክሩ፤ ስለትን ተስለው ስለታቸውን የማይሞሉ፤ በነርሱ ላይ ደንዳና ሰውነት የሚስተዋልባቸው ሰዎች ከናንተ በኋላ ይመጣሉ።"»
[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ አልቡኻሪ - 2651]
ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) በአንድ ዘመን ከሚኖሩ ማህበረሰቦችና ትውልዶች መካከል ምርጡ ማህበረሰብና ትውልድ የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እና ሶሐቦች የነበሩበት ማህበረሰብና ትውልድ መሆኑን ተናገሩ። ቀጥሎ ደግሞ ከዛ ቀጥለው የመጡ የአላህን መልክተኛ ሳያገኙ ሶሓቦችን ያገኙ አማኞች መሆናቸውን ተናገሩ። ቀጥሎ ደግሞ ከዛ ቀጥለው የመጡ አትባዑ ታቢዒኖች ናቸው። ይህን ሐዲሥ የተናገረው ሶሓባ አራተኛው ትውልድ በመጠቀሱ ዙሪያ አመንትቷል። ቀጥለው ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) "ከነዚህ በኋላ ሰው የማይተማመንባቸው ከዳተኞች የሆኑ፤ ለምስክርነት ሳይጠየቁ በፊት ምስክርነትን የሚሰጡ፤ ስለት ተስለው ስለታቸውን የማይሞሉ፤ ውፍረት በግልፅ እስኪስተዋልባቸው ድረስ መብላትና መጠጣት የሚያበዙ ሰዎች ይመጣሉ።" አሉ።