عَنِ المُغِيرَةِ بْنِ شُعْبَةَ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُ عَنِ النَّبِيِّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ قَالَ:
«لاَ يَزَالُ طَائِفَةٌ مِنْ أُمَّتِي ظَاهِرِينَ، حَتَّى يَأْتِيَهُمْ أَمْرُ اللَّهِ وَهُمْ ظَاهِرُونَ».
[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح البخاري: 7311]
المزيــد ...
ከሙጊራ ቢን ሹዕባ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ ብለዋል፦
"ከኡመቴ መካከል የበላይ የሆኑ ጭፍሮች (ከመኖር) አይወገዱም። የአላህ ትእዛዝ እስኪመጣባቸው ድረስም የበላይ እንደሆኑ ይቆያሉ።"
[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ አልቡኻሪ - 7311]
ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ከኡመቴ መካከል በሰዎች ላይ የበላይ የሆኑ፣ በተፃረራቸው ላይ አሸናፊዎች የሆኑ ህዝቦች ከመኖር አይወገዱም። ይህ የበላይነታቸው የሚቆየውም ትንሳኤ ከመቆሙ በፊት የዱንያ መጨረሻ ዘመን ላይ ነፍሳቸው እንድትወጣ የሚመጣው የአላህ ትእዛዝ እስኪመጣ ድረስ መሆኑን ተናገሩ።