عن أنس بن مالك رضي الله عنه قال: قال رسول الله صلى الله عليه وسلم:
«إِنَّ اللهَ لَيَرْضَى عَنِ الْعَبْدِ أَنْ يَأْكُلَ الْأَكْلَةَ فَيَحْمَدَهُ عَلَيْهَا، أَوْ يَشْرَبَ الشَّرْبَةَ فَيَحْمَدَهُ عَلَيْهَا».
[صحيح] - [رواه مسلم] - [صحيح مسلم: 2734]
المزيــد ...
ከአነስ ቢን ማሊክ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ ብሏል: "የአላህ መልክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል፦
'አላህ ባሪያው ምግብን በልቶ እንዲያመሰግነው ወይም መጠጥን ጠጥቶ እንዲያመሰግነው ይወዳል።'"
[ሶሒሕ ነው።] - [ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 2734]
አንድ ባሪያ ጌታውን በቸረውና ባጣቀመው ፀጋዎቹ ምክንያት ማመስገኑ የአላህ ውዴታን ከሚያገኝባቸው ምክንያቶች መካከል አንዱ ስለሆነ ምግብ በልቶም "አልሐምዱሊላህ" ማለት ፤ የሚጠጣም ጠጥቶ "አልሐምዱሊላህ" ማለት እንደሚገባው ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ገለፁ።