+ -

عَنْ عَائِشَةَ أُمِّ المُؤْمِنين رضي الله عنها زَوْجِ النَّبِيِّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ أَنَّ رَسُولَ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ قَالَ:
«يَا عَائِشَةُ إِنَّ اللهَ رَفِيقٌ يُحِبُّ الرِّفْقَ، وَيُعْطِي عَلَى الرِّفْقِ مَا لَا يُعْطِي عَلَى الْعُنْفِ، وَمَا لَا يُعْطِي عَلَى مَا سِوَاهُ».

[صحيح] - [رواه مسلم] - [صحيح مسلم: 2593]
المزيــد ...

የነቢዩ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - ባለቤት ከሆነችው ከአማኞች እናት ዓኢሻህ -አላህ መልካም ስራዋን ይውደድላትና- እንደተላለፈው የአላህ መልክተኛ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - እንዲህ አሉ፦
"ዓኢሻ ሆይ! አላህ ርህሩህ ነው። ለስላሳነትንም ይወዳል። አላህ በግትርነት ላይና ከልስላሴ ውጪ ባሉ መስተጋብሮች ላይ የማይሰጠውንም በልስላሴ ይሰጣል።"

[ሶሒሕ ነው።] - [ሙስሊም ዘግበውታል። - ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 2593]

ትንታኔ

ነቢዩ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - ለአማኞች እናት ለሆነችው ለዓኢሻ -አላህ መልካም ስራዋን ይውደድላትና- በእዝነት ላይ አነሳሷት። አላህ ለባሮቹ ርህሩህና ለስላሳ ነው። ለነርሱ ገርን ይፈልግላቸዋል። ለነርሱ ችግርን አይፈልግም። ከአቅማቸው በላይም አያስገድዳቸውም። የአላህ ባሪያ የሆነም ሰው ገራገር ማንነትን መላበሱንና ገርን መውሰዱን አላህ ይወድለታል። ልበ ደረቅና ስነምግባረ ብልሹ መሆንም የለበትም። አላህ በዱንያ ውስጥ እዝነትና ገራገርነትን ለተላበሰ ሰው ባማረ ሙገሳ ያወሳዋል፣ ፍላጎቱን ያሟላለታል፣ ግቡንም ያሳካለታል። በመጪው ዓለም ደግሞ ትልቅ ምንዳን ይሰጠዋል። ይህም ግትርነት፣ ድርቅናና ሀይለኝነትን ለተላበሰ ሰው ከሚሰጠው የበዛ ምንዳ ነው። ለስላሳነትን መላበስ ሌሎች ባህሪያትን መላበስ የማያመጡትን ጥቅም ይዞ ይመጣል።

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. በለስላሳነት ላይ መነሳሳቱንና ከግትርነት መከልከሉን እንረዳለን።
  2. ከመልካም ስነምግባሮች መካከል የለስላሳነት ደረጃ የላቀ መሆኑን እንረዳለን።
  3. ልስላሴን የተላበሰ ሰው ከአላህ የሆነ መልካም ሙገሳና ትልቅ ምንዳ የተገባው ይሆናል።
  4. ሲንዲይ እንዲህ ብለዋል: "ግትርነት የለስላሳት ተቃራኒ ነው። ማለትም ሁለቱንም የዳዕዋ መንገዶች መጠቀም የሚቻልበት ስፍራ ላይ ሰዎችን በልስላሴና በለዘብተኝነት ወደ ቅናቻ የሚጣራ ሰው በግትርነትና በሃይለኝነት ከሚጣራ ሰው ይሻላል። ያለበለዚያ ግን ቦታው በሚመጥነው የዳዕዋ መንገድ ይሰብካል። እውነተኛውን ሁኔታም የሚያውቀው አላህ ነው።"
ትርጉም: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ስፔንኛ ኢንዶኔዥያኛ ባንጋሊኛ ፈረንሳይኛ ቱርክኛ ሩስያኛ ቦስንያኛ ሲንሃላዊ ህንድኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ቬትናማዊ ታጋሎግ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ስዋሒልኛ ታሚልኛ ታይላንድኛ አሳምኛ الدرية الرومانية المجرية الجورجية الخميرية الماراثية
ትርጉሞችን ይመልከቱ