عن عائشة رضي الله عنها زوج النبي صلى الله عليه وسلم عن النبي صلى الله عليه وسلم قال:
«إِنَّ الرِّفْقَ لَا يَكُونُ فِي شَيْءٍ إِلَّا زَانَهُ، وَلَا يُنْزَعُ مِنْ شَيْءٍ إِلَّا شَانَهُ».

[صحيح] - [رواه مسلم] - [صحيح مسلم: 2594]
المزيــد ...

የነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ባለቤት ከሆነችው ከእናታችን ዓኢሻህ -አላህ መልካም ስራዋን ይውደድላትና- እንደተላለፈው ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል፦
"በአንድ ነገር ውስጥ ገራገርነት (ልስላሴ) አይኖርም ያስዋበው ቢሆን እንጂ ፤ ከአንድ ነገር ውስጥ ደግሞ አይነሳም አስቀያሚ የሚያደርገው ቢሆን እንጂ።"

[ሶሒሕ ነው።] - [ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 2594]

ማብራሪያ

ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም በንግግርም ይሁን በተግባር ገራገርነት፣ ለስላሳነትና እርጋታ ነገሮች ላይ ውበት፣ ምሉዕነትና ማማር የሚጨምሩ ሲሆኑ እንዲሁም ይህንኑ ባህሪ የተላበሰ ሰውም ፍላጎቱን ለማሳካት የተገባ እንደሆነ ገለፁ።
ገራገር (ለስላሳ) አለመሆን ደግሞ ነገሮችን ያነውራቸዋልም አስቀያሚ ያደርጋቸዋልም፤ ስለዚህም ባለቤቱ አላማውን እንዳያገኝ ይከለክለዋል። ካገኘም በችግር ነው የሚያገኘው።

ከሐዲሡ የሚቀሰሙ ቁምነገሮች

  1. ለስላሳ ባህሪን በመላበስ ላይ መበረታታቱን ተረድተናል።
  2. ገራገርነት (ልስላሴ) ሰውን ያስውባል። ገራገርነት በዱንያም (ልስላሴ) በአኺራም የሚገኙ ሁሉም መልካም ጉዳዮችን ለማግኘት ምክንያት ነው።
ትርጉሞችን አሳይ
ቋንቋ: الإنجليزية الأوردية الإسبانية ተጨማሪ (64)