عن عائشة رضي الله عنها قالت: سمعت رسول الله صلى الله عليه وسلم يقول:
«إنَّ المُؤْمِنَ ليُدرِكُ بِحُسْنِ خُلُقِهِ دَرَجَةَ الصَّائِمِ القَائِمِ».

[صحيح بشواهده] - [رواه أبو داود وأحمد] - [سنن أبي داود: 4798]
المزيــد ...

ከእናታችን ዓኢሻህ -አላህ መልካም ስራዋን ይውደድላትና- እንደተላለፈው እንዲህ ብላለች: "የአላህ መልክተኛን ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ሲሉ ሰምቻለሁ፦
'አንድ ሙእሚን በመልካም ስነምግባሩ የፆመኛና (የሌሊት) ሰጋጅን ደረጃ ያገኛል።'"

[በማመሳከሪያዎቹ ሶሒሕ ነው።] - [አቡዳውድና አሕመድ ዘግበውታል።] - [ሱነን አቡዳውድ - 4798]

ማብራሪያ

መልካም ስነምግባርን የተላበሰ ሰው ቀኑን በመፆምና ሌሊቱን በመቆም የዘወተረ ሰውን ደረጃ እንደሚደርስ ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ገለፁ። መልካም ስነምግባር ሲጠቀለል: መልካምን መለገስ፣ ንግግርን ማሳመር፣ ፊትን መፍታት፣ ሰውን ከመጉዳት መቆጠብና የነሱን ክፋት መቻል ነው።

ከሐዲሡ የሚቀሰሙ ቁምነገሮች

  1. ኢስላም ስነምግባርን በማጥራትና በማሟላት ላይ ትልቅ ትኩረት መቸሩን እንረዳለን።
  2. አንድ ሰው በመልካም ስነምግባሩ ቀን ምንም ሳያፈጥር የሚፆምና ምንም ሳይደክም ሌሊቱን የሚቆም ሰው ደረጃ ላይ መድረሱ የመልካም ስነምግባርን ትሩፋት ያስረዳናል።
  3. ቀኑን መፆምና ሌሊቱን መቆም ለነፍስ የሚከብዱ ትልልቅ ስራዎች ናቸው። መልካም ስነምግባርን የተላበሰ ሰው የነርሱን ደረጃ የደረሰው ነፍሱን በመልካም መስተጋብር ላይ ስለታገለ ነው።
ትርጉሞችን አሳይ
ቋንቋ: الإنجليزية الأوردية الإسبانية ተጨማሪ (64)