عَنِ ابْنِ عَبَّاسٍ رَضيَ اللهُ عنهما قَالَ:
قَالَ رَسُولُ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ لِلْأَشَجِّ أَشَجِّ عَبْدِ الْقَيْسِ: «إِنَّ فِيكَ خَصْلَتَيْنِ يُحِبُّهُمَا اللهُ: الْحِلْمُ، وَالْأَنَاةُ».
[صحيح] - [رواه مسلم] - [صحيح مسلم: 17]
المزيــد ...
ከኢብኑ ዐባስ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ ብለዋል:
«የአላህ መልክተኛ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - ለአሸጅ ዐብዲል ቀይስ እንዲህ አሉ: "አንተ ውስጥ ሁለት አላህ የሚወዳቸው ነገሮች አሉ። እነርሱም አስተዋይነትና መረጋጋት ናቸው።"»
[ሶሒሕ ነው።] - [ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 17]
ነቢዩ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - የዐብዱል ቀይስ የሚባል ጎሳ መሪ ለሆነው ለሙንዚር ቢን ዓኢዝ አሸጅ -አላህ መልካም ስራውን ይውደድለትና- እንዲህ አሉት: አንተ ውስጥ አላህ የሚወዳቸው ሁለት ባህሪያት አሉ። እነርሱም: አስተዋይነት፣ ማረጋገጥ፣ እርጋታና አለመቸኮል ናቸው።