+ -

عَنْ عُقْبَةَ بْنِ عَامِرٍ رضي الله عنه قَالَ:
قُلْتُ: يَا رَسُولَ اللهِ مَا النَّجَاةُ؟ قَالَ: «امْلِكْ عَلَيْكَ لِسَانَكَ، وَلْيَسَعْكَ بَيْتُكَ، وَابْكِ عَلَى خَطِيئَتِكَ».

[صحيح] - [رواه الترمذي وأحمد] - [سنن الترمذي: 2406]
المزيــد ...

ከዑቅባህ ቢን ዓሚር (ረዲየሏሁ ዐንሁ) -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላችውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ፦
«የአላህ መልክተኛ ሆይ! መዳኛ ምንድን ነው? አልኳቸው። እርሳቸውም "ምላስህን ተቆጣጠር፤ ቤትህ ይስፋህ፤ በወንጀልህም ላይ አልቅስ!" አሉ።»

[ሶሒሕ ነው።] - [ቲርሚዚና አሕመድ ዘግበውታል።] - [ሱነን ቲርሚዚ - 2406]

ትንታኔ

ዑቅባህ ቢን ዓሚር (ረዲየሏሁ ዐንሁ) -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላችውና- ነቢዩን (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ሙእሚን በዱንያም ሆነ በመጪው ዓለም ስለሚድንባቸው ሰበቦች ጠየቀ።
ነቢዩም (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና በሶስት ነገሮች ላይ አደራ አሉት።
የመጀመሪያው: ምንም መልካምነት ከሌለው ነገርና መጥፎ የተባለን ንግግር ሁሉ ከመናገር ምላስህን ቆጥብ! ከመልካም በቀር ምንም አትናገር።
ሁለተኛው: አላህን ለብቻህ ለማምለክ ቤትህ አዘውትር! አላህን በማምለክ ተጠመድ! ከፈተናዎች በቤትህ ተከለል።
ሶስተኛው: ከሰራኸው ወንጀል ተመለስ፣ ተፀፀት፣ አልቅስ!

ትርጉም: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ስፔንኛ ኢንዶኔዥያኛ ኡይጙራዊ ባንጋሊኛ ፈረንሳይኛ ቱርክኛ ሩስያኛ ቦስንያኛ ሲንሃላዊ ህንድኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ቬትናማዊ ታጋሎግ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ማላያላምኛ ስዋሒልኛ ታይላንድኛ ቡሽትኛ አሳምኛ الهولندية الغوجاراتية النيبالية
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. ሰሐቦች (ረዲየሏሁ ዐንሁም) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - የመዳኛን መንገድ ለማወቅ ያላቸውን ጉጉት እንረዳለን።
  2. በዱንያም ሆነ በመጪው አለም መዳኛ የሆኑ ሰበቦች መገለጻቸው።
  3. አንድ ሰው ሌላውን መጥቀም ያቃተው ጊዜ ወይም ከሰዎች ጋር መቀላቀሉ ሃይማኖቱንም ይሁን ነፍሱን ጉዳት እንደሚጎዳው ከሰጋ በራሱ ላይ ብቻ እንዲጠመድ መነሳሳቱን እንረዳለን።
  4. ቤት ላይ ትኩረት ማድረግ ‐ በተለይ በፈተና ወቅት ‐ መጠቆሙ። ቤት ውስጥ ማሳለፍ ሃይማኖትን ለመጠበቅ ከሚረዱ መንገዶች አንዱ ነው።