عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ رضي الله عنه قَالَ:
قَالَ رَسُولُ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ: «يَقُولُ اللهُ عَزَّ وَجَلَّ: أَنَا عِنْدَ ظَنِّ عَبْدِي، وَأَنَا مَعَهُ حِينَ يَذْكُرُنِي، فَإِنْ ذَكَرَنِي فِي نَفْسِهِ ذَكَرْتُهُ فِي نَفْسِي، وَإِنْ ذَكَرَنِي فِي مَلَإٍ ذَكَرْتُهُ فِي مَلَإٍ خَيْرٍ مِنْهُ، وَإِنِ اقْتَرَبَ إِلَيَّ شِبْرًا، تَقَرَّبْتُ إِلَيْهِ ذِرَاعًا، وَإِنِ اقْتَرَبَ إِلَيَّ ذِرَاعًا، اقْتَرَبْتُ إِلَيْهِ بَاعًا، وَإِنْ أَتَانِي يَمْشِي أَتَيْتُهُ هَرْوَلَةً».
[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح مسلم: 2675]
المزيــد ...
ከአቡ ሁረይራ (ረዲየላሁ ዐንሁ) -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ:
«የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ብለዋል "አላህ እንዲህ አለ: እኔ ባሪያዬ ባሰበኝ በኩል ነኝ። ባስታወሰኝም ጊዜ እኔ ከርሱ ጋር ነኝ። ለብቻው ካወሳኝ ለብቻዬ አወሳዋለሁ፤ በህብረት ካወሳኝ ደሞ ከርሱ የተሻለ በሆኑ ህብረቶች ዘንድ አወሳዋለሁ። አንድ ስንዝር ወደኔ ከቀረበ አንድ ክንድ ወደርሱ እቀርባለሁ። አንድ ክንድ ወደኔ ከቀረበ እጅ ሙሉ ወደርሱ እቀርባለሁ። እየተራመደ ወደኔ ከመጣ በሶምሶማ ወደርሱ እመጣለሁ።"»
[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 2675]
ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና አላህ እንዲህ ማለቱን ተናገሩ:
እኔ ባሪያዬ እኔን ባሰበኝ በኩል ነኝ። ባሪያዬ ስለኔ ባለው እሳቤ አስተናግደዋለሁ። ይህም ተስፋ በማድረግ፣ ይቅርታዬን በመመኘት ነው። መልካምም ሆነ ከዛ ውጪ ከኔ ተስፋ ያደረገውን ከኔ ያገኛል። እኔን ካወሳኝ በእዝነቴ፣ በመግጠም፣ በመምራት፣ በመጠበቅና በማገዝ ከርሱ ጋር እሆናለሁ።
ለብቻው ተገልሎ በ"ተስቢሕ"፣ በ"ተህሊል" ወይም በሌሎች ዚክሮች ካወሳኝ ለብቻዬ አወሳዋለሁ።
በህብረት ካወሳኝ እርሱ እኔን ካወሳበት ህብረት በተሻለና በበዛ ምርጥ ህብረት እርሱን አወሳዋለሁ።
ወደ አላህ የስንዝር ያህል ለተቃረበ ሰው አላህም ጨምሮ የክንድ ያህል ወደርሱ ይቀርባል።
ክንድ ያህል ወደርሱ ከተቃረበ አላህም ሁለት ክንድ የሚያህል ወደርሱ ይቀርባል።
እየተራመደ ወደ አላህ ከመጣ አላህም ወደርሱ በሶምሶማ ይመጣል።
አንድ ባሪያ አላህን በመታዘዝና ወደርሱ በመዞር የተቃረበ ጊዜ በሰራው ስራ ትይዩ ለመመንዳት ጌታም ወደርሱ መቃረብን ይጨምርለታል።
አንድ አማኝ ለጌታው ያለው ባርነት በተሟላ ቁጥር አላህም ወደርሱ ይቀርባል። የአላህ ስጦታና ምንዳ ከባሪያው ስራና ጥንካሬ የበለጠ ነው። ዋናው ፍሬ ሀሳብ በቁጥርም ሆነ ሁኔታ የአላህ ምንዳ ከስራ ታመዝናለች የሚለው ነው።
አማኝ የሆነ ሰው በአላህ ላይ ያለውን እሳቤ ያሳምራል። አላህን እስኪገናኝ ድረስም ይጨምራልም ይፈጥናልም።