+ -

عَنْ عَبْدِ اللَّهِ بْنِ عُمَرَ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُمَا:
أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ قَالَ وَهُوَ عَلَى المِنْبَرِ، وَذَكَرَ الصَّدَقَةَ، وَالتَّعَفُّفَ، وَالمَسْأَلَةَ: «اليَدُ العُلْيَا خَيْرٌ مِنَ اليَدِ السُّفْلَى، فَاليَدُ العُلْيَا: هِيَ المُنْفِقَةُ، وَالسُّفْلَى: هِيَ السَّائِلَةُ».

[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح البخاري: 1429]
المزيــد ...

ከዐብደላህ ቢን ዑመር -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ:
«የአላህ መልክተኛ - የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - ሚንበር ላይ ሳሉ ስለ ምፅዋት፣ ጥብቅነትና ልመና ካወሱ በኋላ እንዲህ አሉ: "ከላይ ያለች እጅ ከታች ካለች እጅ የተሻለች ናት። ከላይ ያለች እጅ ሰጪዋ ስትሆን ከታች ደግሞ ጠያቂዋ እጅ ናት።"»

[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ አልቡኻሪ - 1429]

ትንታኔ

ነቢዩ - የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - ሚንበር ላይ ኹጥባ እያደረጉ ሳሉ ስለ ምፅዋት፣ ጥብቅነትና ልመና ካወሱ በኋላ እንዲህ አሉ: "የምትሰጥ የሆነች ከላይ ያለች እጅ የምትለምን ከሆነች ከታች ካለች እጅ አላህ ዘንድ የተሻለችና ተወዳጅ ናት።"

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. ከዚህ ሐዲሥ ለመልካም መንገዶች የመስጠትና የመመፅወትን ትሩፋትና የመለመንን አስከፊነት እንረዳለን።
  2. በዚህ ሐዲሥ ከልመና መጠበቅ፣ ከሰዎች መብቃቃት፣ ከፍ ያሉ ነገሮችን እንድንላበስና የወረደን ነገር እንድንተው ተበረታቷል። አላህ ከፍ ያሉ ነገሮችን ይወዳል።
  3. እጆች አራት አይነት ናቸው። በደረጃም የሚበላለጡት እንደሚከተለው ነው: ከፍተኛዋ ሰጪ ናት። ቀጥሎ ከመቀበል የተብቃቃች እጅ ናት። ቀጥሎ ሳትለምን የምትቀበል እጅ ናት። ቀጥሎ የመጨረሻዋ የምትለምን እጅ ናት።
ትርጉም: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ስፔንኛ ኢንዶኔዥያኛ ኡይጙራዊ ባንጋሊኛ ፈረንሳይኛ ቱርክኛ ሩስያኛ ቦስንያኛ ሲንሃላዊ ህንድኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ቬትናማዊ ታጋሎግ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ስዋሒልኛ ታሚልኛ ታይላንድኛ አሳምኛ الدرية الرومانية المجرية الجورجية الخميرية الماراثية
ትርጉሞችን ይመልከቱ
ተጨማሪ