+ -

عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُ:
أَنَّ أَعْرَابِيًّا أَتَى النَّبِيَّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ، فَقَالَ: دُلَّنِي عَلَى عَمَلٍ إِذَا عَمِلْتُهُ دَخَلْتُ الجَنَّةَ، قَالَ: «تَعْبُدُ اللَّهَ لاَ تُشْرِكُ بِهِ شَيْئًا، وَتُقِيمُ الصَّلاَةَ المَكْتُوبَةَ، وَتُؤَدِّي الزَّكَاةَ المَفْرُوضَةَ، وَتَصُومُ رَمَضَانَ» قَالَ: وَالَّذِي نَفْسِي بِيَدِهِ لاَ أَزِيدُ عَلَى هَذَا، فَلَمَّا وَلَّى قَالَ النَّبِيُّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ: «مَنْ سَرَّهُ أَنْ يَنْظُرَ إِلَى رَجُلٍ مِنْ أَهْلِ الجَنَّةِ، فَلْيَنْظُرْ إِلَى هَذَا».

[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح البخاري: 1397]
المزيــد ...

ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው:
"አንድ የገጠር ሰው ወደ ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) በመምጣት እንዲህ አለ: ' ብሰራው ጀነት የምገባበትን ስራ ጠቁሙኝ!' እርሳቸውም እንዲህ አሉት 'በርሱ ላይ አንዳችም ሳታጋራበት አሏህን ማምለክ፣ ግዴታ ሶላትን መስገድ፣ ግዴታ የሆነውን ዘካ መስጠት፣ ረመዷንን መጾም ነው።' እርሱም "ነፍሴ በእጁ በሆነችው እምላለሁ! ከዚህ ምንም አልጨምርም።' ብሎ ዞሮ የሄደ ጊዜ ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ አሉ፦ 'ከጀነት ባለቤቶች የሆነን ሰው መመልከት ያስደሰተው ወደዚህ ሰውዬ ይመልከት።' አሉ።"

[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ አልቡኻሪ - 1397]

ትንታኔ

(መኖሪያው) ገጠራማ ስፍራ የሆነ አንድ ሰው ጀነት የሚያስገባውን ስራ እንዲጠቁሙት ወደ ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና መጣ። ነቢዩም (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ጀነት መግባትና ከእሳት መዳን የኢስላም ማእዘናትን በመፈፀም ላይ የተገደበ እንደሆነ መለሱለት። አላህን በብቸኝነት መገዛትና በርሱ ላይ አንዳችንም አለማጋራት፣ በሁሉም ቀንና ምሽቶች አላህ በባሮቹ ላይ ግዴታ ያደረገውን አምስቱን ሶላቶች መስገድ፣ አላህ በአንተ ላይ ግዴታ ያደረገውን የገንዘብ ዘካ ለሚገባው ሰው መስጠት፣ የረመዷን ወርን በወቅቱ በመጾም ላይ መጠባበቅ ናቸው። ሰውዬውም "ነፍሴ በእጁ በሆነችው እምላለሁ! ከእርሶ ከሰማሁት ግዴታ አምልኮዎች አንዳችም ስራ አልጨምርምም አልቀንስምም።" አለ። ዞሮ የሄደ ጊዜም ነቢዩ ( የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ አሉ: "ከጀነት ባለቤቶች መካከል የሆነን ሰው መመልከት ያስደሰተው ወደዚህ ባላገር (የገጠር) ሰውዬ ይመልከት።"

ትርጉም: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ስፔንኛ ኢንዶኔዥያኛ ኡይጙራዊ ባንጋሊኛ ፈረንሳይኛ ቱርክኛ ሩስያኛ ቦስንያኛ ሲንሃላዊ ህንድኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ቬትናማዊ ታጋሎግ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ማላያላምኛ ቴልጉ ስዋሒልኛ ታይላንድኛ ቡሽትኛ አሳምኛ አልባንኛ السويدية الهولندية الغوجاراتية Kyrgyzisht النيبالية Jorubisht الليتوانية الدرية الصربية الصومالية Kinjaruandisht الرومانية التشيكية Malagasisht Oromisht Kannadisht الولوف الأوكرانية
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. ወደ አላህ በሚደረግ ጥሪ ላይ መጀመሪያ የሚጀመረው አላህን በአምልኮ በመነጠል ነው።
  2. አዲስ ሰለምቴ ለሆነ ሰው ግዴታ የሆኑበትን ጉዳዮች ብቻ በማስተማር መብቃቃት እንደሚገባ እንረዳለን።
  3. ወደ አላህ የሚደረግ ዳዕዋ የግድ ደረጃ በደረጃ መሆን እንደሚገባው እንረዳለን።
  4. የዲንን ጉዳይ በመማር ላይ የሰውዬውን ጉጉት እንረዳለን።
  5. አንድ ሙስሊም በግዴታ ነገሮች ላይ ብቻ ቢገደብም እንደሚድን እንረዳለን። ይህ ግን በትርፍ አምልኮዎች ላይ መሳነፍ ይገባል ማለት አይደለም። ምክንያቱም ትርፍ ስራዎች ግዴታዎች ላይ ያሉ ጉድለቶችን ይሞላሉና።
  6. የተወሰኑ አምልኮዎች ብቻ ተነጥለው መወሳታቸው አንገብጋቢነታቸውንና በነዛ አምልኮዎች ላይ መነሳሳቱን ይጠቁማል እንጂ ግዴታ የሆኑ ሌሎች አምልኮዎች እንደሌሉ አይጠቁምም።