عَنْ أَبِي سَعِيدٍ الخُدْرِيِّ رضي الله عنه أَنَّهُ سَمِعَ رَسُولَ اللَّهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ يَقُولُ:
«إِذَا رَأَى أَحَدُكُمُ الرُّؤْيَا يُحِبُّهَا فَإِنَّهَا مِنَ اللَّهِ، فَلْيَحْمَدِ اللَّهَ عَلَيْهَا وَلْيُحَدِّثْ بِهَا، وَإِذَا رَأَى غَيْرَ ذَلِكَ مِمَّا يَكْرَهُ، فَإِنَّمَا هِيَ مِنَ الشَّيْطَانِ، فَلْيَسْتَعِذْ مِنْ شَرِّهَا، وَلاَ يَذْكُرْهَا لِأَحَدٍ، فَإِنَّهَا لَنْ تَضُرَّهُ».
[صحيح] - [رواه البخاري] - [صحيح البخاري: 7045]
المزيــد ...
ከአቡ ሰዒድ አልኹድሪይ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: እርሱ የአላህ መልዕክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ሲሉ ሰምቷል፦
"አንዳችሁ የሚወደውን ህልም በተመለከተ ጊዜ እርሷ ከአላህ ናትና በርሷ ምክንያት አላህን ያመስግንም ለሌሎችም ያውራት፤ ከዚህ ውጪ የሚጠላውን ህልም የተመለከተ ጊዜ ደሞ እርሷ ከሸይጧን ናትና ከክፋቷ በአላህ ይጠበቅ፤ ለአንድም ሰው አያውራ። እርሷም አትጎዳውም።"
[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪ ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ አልቡኻሪ - 7045]
ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና የሚያስደስት መልካም ህልም ማየት ከአላህ እንደሆነ ተናገሩ። በርሱም ላይ አላህን እንዲያመሰግንና ስለርሱም እንዲናገር ጠቆሙ። የሚጠላውንና የሚያሳዝነውን ህልም ያየ ጊዜ ደግሞ ከሸይጧን ነውና ከክፋቱ በአላህ እንዲጠበቅና ለአንድም ሰው እንዳያወራም ጠቆሙ። ህልምን ተከትሎ ከሚመጡ ጎጂ ነገሮች ሰላም ለመሆን ከላይ የተጠቀሰውን ማድረግ አላህ ሰበብ ስላደረገው ምንም አይጎዳውም።