عن جَابِرِ بْنِ عَبْدِ اللَّهِ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُمَا، قَالَ:
كَانَ رَسُولُ اللَّهِ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ يُعَلِّمُنَا الِاسْتِخَارَةَ فِي الْأُمُورِ كَمَا يُعَلِّمُنَا السُّورَةَ مِنَ الْقُرْآنِ، يَقُولُ: «إِذَا هَمَّ أَحَدُكُمْ بِالْأَمْرِ فَلْيَرْكَعْ رَكْعَتَيْنِ مِنْ غَيْرِ الْفَرِيضَةِ، ثُمَّ لِيَقُلِ: اللَّهُمَّ إِنِّي أَسْتَخِيرُكَ بِعِلْمِكَ وَأَسْتَقْدِرُكَ بِقُدْرَتِكَ، وَأَسْأَلُكَ مِنْ فَضْلِكَ الْعَظِيمِ، فَإِنَّكَ تَقْدِرُ وَلَا أَقْدِرُ، وَتَعْلَمُ وَلَا أَعْلَمُ، وَأَنْتَ عَلَّامُ الْغُيُوبِ، اللَّهُمَّ إِنْ كُنْتَ تَعْلَمُ أَنَّ هَذَا الْأَمْرَ خَيْرٌ لِي فِي دِينِي، وَمَعَاشِي، وَعَاقِبَةِ أَمْرِي» أَوْ قَالَ: «عَاجِلِ أَمْرِي وَآجِلِهِ، فَاقْدُرْهُ لِي وَيَسِّرْهُ لِي ثُمَّ بَارِكْ لِي فِيهِ، وَإِنْ كُنْتَ تَعْلَمُ أَنَّ هَذَا الْأَمْرَ شَرٌّ لِي فِي دِينِي وَمَعَاشِي وَعَاقِبَةِ أَمْرِي» أَوْ قَالَ: «فِي عَاجِلِ أَمْرِي وَآجِلِهِ، فَاصْرِفْهُ عَنِّي وَاصْرِفْنِي عَنْهُ، وَاقْدُرْ لِي الْخَيْرَ حَيْثُ كَانَ، ثُمَّ أَرْضِنِي» قَالَ: «وَيُسَمِّي حَاجَتَه».
[صحيح] - [رواه البخاري] - [صحيح البخاري: 1162]
المزيــد ...
ከጃቢር ቢን ዐብደላህ (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላችውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ:
«የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) የቁርአን ምዕራፍ እንደሚያስተምሩን ለጉዳያችን ኢስቲኻራን (አላህን የማማረጥን ዱዓ) እንዴት እንደምናደርግም ያስተምሩን ነበር። እንዲህም ይሉን ነበር: "አንዳችሁ አንድ ጉዳይ ያሰበ ጊዜ ግዴታ ከሆነ ሶላት ውጪ ሁለት ረከዓ ይስገድና እንዲህ ይበል: "አሏሁመ ኢኒ አስተኺሩከ ቢዒልሚክ ወአስተቅዲሩከ ቢቁድረቲክ ወአስአሉከ ሚን ፈድሊከል ዐዚም ፈኢንነከ ተቅዲሩ ወላ አቅዲር ወታዕለሙ ወላ አዕለሙ ወአንተ ዐላሙል ጙዩብ አሏሁመ ኢን ኩንተ ተዕለሙ አነ ሀዛል አምር ኸይሩን ሊ ፊ ዲኒ ወመዓሺ ወዓቂበቲ አምሪ" ወይም ደግሞ፡ "… አሏሁመ ኢን ኩንተ ተዕለሙ አነ ሀዛል አምር ኸይሩን ሊ ፊዓጂሊ አምሪ ወአጂሊሂ ፈስሪፍሁ ዓኒ ወስሪፍኒ ዓንሁ ወቅዱር ሊየል ኸይረ ሓይሡ ካነ ሡመርዲኒ" ይበል፤ ጉዳዩንም በስሙ ለይቶ ይግለፀው። አሉ።» (ትርጉሙም: "አላህ ሆይ! እኔ በዕውቀትህ አማርጥሃለሁ፣ በችሎታህ አቅምን እንድትሰጠኝ እጠይቅሃለሁ። ከትልቁ ችሮታህም እጠይቅሃለሁ። አንተ ትችላለህ እኔ አልችልም። አንተ ታውቃለህ እኔ አላውቅም። አንተ የሩቅን አዋቂ ነህ። አላህ ሆይ ይህ ጉዳይ ለሃይማኖቴ፣ ለኑሮዬና ለጉዳዬ መዳረሻ ወይም ለቅርቡም ለወደፊቱም ጉዳዬ ለኔ መልካም መሆኑን ካወቅክ ለኔ ወስንልኝ አቅልልልኝም ከዚያም ለኔ በርሱ ባርክልኝ። ይህ ጉዳይ ለሃይማኖቴ፣ ለኑሮዬና ለጉዳዬ መዳረሻ ወይም ለቅርቡም ለወደፊቱም ጉዳዬ ለኔ መጥፎ መሆኑን ካወቅክ ደግሞ ከኔ ዞር አድርግልኝም እኔንም ከርሱ ዞር አድርገኝ። መልካሙንም ካለበት ቦታ ወስንልኝ ከዚያም እንድወደው አድርገኝ።" ማለት ነው።»
[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪ ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ አልቡኻሪ - 1162]
አንድ ሙስሊም ትክክሉ የቱ እንደሆነ የማያውቀው የሆነን ጉዳይ መፈፀም የፈለገ ጊዜ ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ሶሐቦቻቸውን - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - የቁርአን አንድ ምዕራፍ እንደሚያስተምሯቸው ሁሉ ያስተማሯቸውን የነበረውን ይህንን ሶላት "ሶላተል ኢስቲኻራ"ን መስገድ ይደነገግለታል። ከግዴታ ሶላት ውጪ የሆነን ሁለት ረከዓ ይሰግድና ከዚያም አላህን እንዲህ በማለት ዱዓ ያደርጋል: "አልላሁመ ኢንኒ አስተኺሩከ" አላህ ሆይ! ከሁለቱ ጉዳዮች ለተሻለው እንድትገጥመኝ እፈልጋለሁ። "ቢዒልሚከ" ሁሉንም ነገር ባካባበው ሰፊ በሆነው እውቀትህም እጠይቅሃለሁ። "ወአስተቅዲሩከ ቢቁድረቲከ" በአንተ ካልሆነ በቀር ሀይልም ሆነ ብልሃት የለኝምና ፅኑ በሆነችው ችሎታህ ቻይ እንድታደርገኝ እጠይቅሃለሁ። አንተን ምንም አያቅትህምና። "ወአስአሉከ ሚንፈድሊከል ዐዚም" ሰፊ በሆነው በጎነትህ እጠይቅሃለሁ። የምትለግሰን ስጦታ ከአንተ የሆነ ችሮታ ነው። ለአንድም ሰው ፀጋህን የመዋል ግዴታ የለብህምና። "ፈኢንነከ ተቅዲር" አንተ በሁሉም ነገር ላይ ቻይ ነህና። እኔ ደግሞ ደካማ ነኝ። እኔ ደሞ "ወላአቅዲሩ" ያላንተ እገዛ አንድም ነገር ማድረግ አልችልም። "ወተዕለሙ" አንተ ውጫዊውንም ውስጣዊውንም፣ መልካሙንም መጥፎውንም ነገር አካባቢና ጠቅላይ በሆነ እውቀትህ ታውቃለህ። "ወላአዕለሙ" እኔ ደግሞ በአንተ መግጠምና መምራት ካልሆነ በቀር አንድም ነገር አላውቅም። "ወአንተ ዐላሙል ጉዩብ" አንተ የሩቅን አዋቂ ነህ። ጠቅላይ እውቀትና ፅኑ ችሎታ የአንተ ብቻ ነው። አንተ የወሰንክለትና ያስቻልከው ሰው ካልሆነ በቀር ከአንተ ውጪ ማንም ችሎታ የለውም። ቀጥሎ ይህ ዱዓ አድራጊ ሙስሊም ጉዳዩን እየጠቀሰ እንዲህ በማለት ዱዓ ያደርጋል። "አልላሁምመ" አላህ ሆይ! እኔ ጉዳዬን ወዳንተ አስጠግቻለሁ። "ኢንኩንተ ተዕለሙ" ስለዚህ ጉዳይ (ጉዳዩን በስሙ እየገለፀ) ባለህ እውቀትህ የምታውቀው ‐ ለምሳሌ:- ይህን ቤት መግዛቴ ወይም ይህን መኪና መግዛቴ ወይም ይህቺን ሴት ማግባቴ ወይም ከዚህ ውጪ ያለ ወዘተ ይህ ጉዳይ ቀዳሚ በሆነው ዕውቀትህ "ኸይሩን ሊ ፊ ዲኒ" ለኔ የነገሮቼ መጠበቂያ ለሆነው ሃይማኖቴ የሚበጀኝ ከሆነ "ወመዓሺ" ለዱንያዬ ኑሮ የሚበጀኝ ከሆነ "ወዓቂበቱ አምሪ" ወደፊት ለሚያመራው ጉዳዬ ወይም እርሳቸው ያሉት "ፊ ዓጂሊ አምሪ ወአጂሊህ" ለዱንያዬም ሆነ ለመጪው አለሜ የሚበጀኝ ከሆነ "ፈቅዱርሁ ሊ" ወስንልኝ፣ አዘጋጅልኝ፣ ተፈፃሚ አድርግልኝ። "ወየሲርሁ ሊ ሡመ ባሪክ ሊ ፊህ" ለኔ አግራልኝ ከዚያም መልካሙን በማብዛትም ባርክልኝ። "ወኢንኩንተ ተዕለሙ" አላህ ሆይ! ስለጉዳዬ ባለህ እውቀት የምታውቀው "አንነ ሀዘል አምር" ይህ የማማርጥህ ጉዳይ "ሸሩን ሊ ፊ ዲኒ ወመዓሺ ወዓቂበቲ አምሪ" ወይም እርሳቸው ያሉት "ፊ ዓጂሊ አምሪ ወአጂሊህ ፈስሪፍሁ ዓኒ ወስሪፍኒ ዐንሁ ወቅዱር ሊ አልኸይረ ሐይሡ ካነ ሡመ አርዲኒ ቢህ" ለሃይማኖቴ፣ ለኑሮዬና ለጉዳዬ መዳረሻ ወይም ለቅርቡም ለወደፊቱም ጉዳዬ ለኔ መጥፎ መሆኑን ካወቅክ ደግሞ ከኔ ዞር አድርግልኝም እኔንም ከርሱ ዞር አድርገኝ። መልካሙንም ካለበት ቦታ ወስንልኝ ከዚያም በምወደውም ሆነ በምጠላው ውሳኔዎችህ ባጠቃላይ እንድወደው አድርገኝ።