عَنْ صُهَيْبٍ رضي الله عنه قَالَ: قَالَ رَسُولُ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ:
«عَجَبًا لِأَمْرِ الْمُؤْمِنِ، إِنَّ أَمْرَهُ كُلَّهُ خَيْرٌ، وَلَيْسَ ذَاكَ لِأَحَدٍ إِلَّا لِلْمُؤْمِنِ، إِنْ أَصَابَتْهُ سَرَّاءُ شَكَرَ، فَكَانَ خَيْرًا لَهُ، وَإِنْ أَصَابَتْهُ ضَرَّاءُ صَبَرَ، فَكَانَ خَيْرًا لَهُ».
[صحيح] - [رواه مسلم] - [صحيح مسلم: 2999]
المزيــد ...
ከሱሀይብ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል:
"የአማኝ ነገር ይደንቃል። ሁሉ ነገሩ መልካም ነው። ይህም ለአማኝ እንጂ ለሌላ ለአንድም አካል ሊሆን አይችልም። ደስታ በሚያጋጥመው ጊዜ ያመሰግንና ለርሱ መልካም ይሆንለታል። ጉዳት በሚያጋጥመውም ጊዜ ይታገስና ለርሱ መልካም ይሆንለታል።"»
[ሶሒሕ ነው።] - [ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 2999]
ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) አድናቆታዊ በሆነ መልኩ በአማኝ ጉዳይና ሁኔታ ይገረማሉ። ይህም የአማኝ ሁኔታዎች ባጠቃላይ መልካም በመሆናቸው ነው። ይህም ለአማኝ እንጂ ለሌላ አይሆንም። አማኝ የሆነ ሰው ደስታ በሚያጋጥመው ጊዜ በርሱ ላይ አላህን ያመሰግናል። በማመስገኑም ምንዳን ያገኛል። ጉዳት ሲያጋጥመው ደግሞ ይታገሳልም አላህ ዘንድ ምንዳ አገኝበታለሁ ብሎም ያስባል። በትእግሰቱም ምንዳን ያገኛል። ስለዚህ እርሱ በሁሉም ሁኔታዎቹ በምንዳ ላይ ነው።