عَنْ صُهَيْبٍ رَضيَ اللهُ عنه أَنَّ رَسُولَ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ قَالَ:
"كَانَ مَلِكٌ فِيمَنْ كَانَ قَبْلَكُمْ، وَكَانَ لَهُ سَاحِرٌ، فَلَمَّا كَبِرَ، قَالَ لِلْمَلِكِ: إِنِّي قَدْ كَبِرْتُ، فَابْعَثْ إِلَيَّ غُلَامًا أُعَلِّمْهُ السِّحْرَ، فَبَعَثَ إِلَيْهِ غُلَامًا يُعَلِّمُهُ، فَكَانَ فِي طَرِيقِهِ إِذَا سَلَكَ رَاهِبٌ فَقَعَدَ إِلَيْهِ وَسَمِعَ كَلَامَهُ، فَأَعْجَبَهُ، فَكَانَ إِذَا أَتَى السَّاحِرَ مَرَّ بِالرَّاهِبِ وَقَعَدَ إِلَيْهِ، فَإِذَا أَتَى السَّاحِرَ ضَرَبَهُ، فَشَكَا ذَلِكَ إِلَى الرَّاهِبِ، فَقَالَ: إِذَا خَشِيتَ السَّاحِرَ، فَقُلْ: حَبَسَنِي أَهْلِي، وَإِذَا خَشِيتَ أَهْلَكَ فَقُلْ: حَبَسَنِي السَّاحِرُ، فَبَيْنَمَا هُوَ كَذَلِكَ إِذْ أَتَى عَلَى دَابَّةٍ عَظِيمَةٍ قَدْ حَبَسَتِ النَّاسَ، فَقَالَ: الْيَوْمَ أَعْلَمُ آلسَّاحِرُ أَفْضَلُ أَمِ الرَّاهِبُ أَفْضَلُ؟ فَأَخَذَ حَجَرًا، فَقَالَ: اللهُمَّ إِنْ كَانَ أَمْرُ الرَّاهِبِ أَحَبَّ إِلَيْكَ مِنْ أَمْرِ السَّاحِرِ فَاقْتُلْ هَذِهِ الدَّابَّةَ، حَتَّى يَمْضِيَ النَّاسُ، فَرَمَاهَا فَقَتَلَهَا، وَمَضَى النَّاسُ، فَأَتَى الرَّاهِبَ فَأَخْبَرَهُ، فَقَالَ لَهُ الرَّاهِبُ: أَيْ بُنَيَّ أَنْتَ الْيَوْمَ أَفْضَلُ مِنِّي، قَدْ بَلَغَ مِنْ أَمْرِكَ مَا أَرَى، وَإِنَّكَ سَتُبْتَلَى، فَإِنِ ابْتُلِيتَ فَلَا تَدُلَّ عَلَيَّ، وَكَانَ الْغُلَامُ يُبْرِئُ الْأَكْمَهَ وَالْأَبْرَصَ، وَيُدَاوِي النَّاسَ مِنْ سَائِرِ الْأَدْوَاءِ، فَسَمِعَ جَلِيسٌ لِلْمَلِكِ كَانَ قَدْ عَمِيَ، فَأَتَاهُ بِهَدَايَا كَثِيرَةٍ، فَقَالَ: مَا هَاهُنَا لَكَ أَجْمَعُ، إِنْ أَنْتَ شَفَيْتَنِي، فَقَالَ: إِنِّي لَا أَشْفِي أَحَدًا إِنَّمَا يَشْفِي اللهُ، فَإِنْ أَنْتَ آمَنْتَ بِاللهِ دَعَوْتُ اللهَ فَشَفَاكَ، فَآمَنَ بِاللهِ فَشَفَاهُ اللهُ، فَأَتَى الْمَلِكَ فَجَلَسَ إِلَيْهِ كَمَا كَانَ يَجْلِسُ، فَقَالَ لَهُ الْمَلِكُ: مَنْ رَدَّ عَلَيْكَ بَصَرَكَ؟ قَالَ: رَبِّي، قَالَ: وَلَكَ رَبٌّ غَيْرِي؟ قَالَ: رَبِّي وَرَبُّكَ اللهُ، فَأَخَذَهُ فَلَمْ يَزَلْ يُعَذِّبُهُ حَتَّى دَلَّ عَلَى الْغُلَامِ، فَجِيءَ بِالْغُلَامِ، فَقَالَ لَهُ الْمَلِكُ: أَيْ بُنَيَّ قَدْ بَلَغَ مِنْ سِحْرِكَ مَا تُبْرِئُ الْأَكْمَهَ وَالْأَبْرَصَ، وَتَفْعَلُ وَتَفْعَلُ، فَقَالَ: إِنِّي لَا أَشْفِي أَحَدًا، إِنَّمَا يَشْفِي اللهُ، فَأَخَذَهُ فَلَمْ يَزَلْ يُعَذِّبُهُ حَتَّى دَلَّ عَلَى الرَّاهِبِ، فَجِيءَ بِالرَّاهِبِ، فَقِيلَ لَهُ: ارْجِعْ عَنْ دِينِكَ، فَأَبَى، فَدَعَا بِالْمِئْشَارِ، فَوَضَعَ الْمِئْشَارَ فِي مَفْرِقِ رَأْسِهِ، فَشَقَّهُ حَتَّى وَقَعَ شِقَّاهُ، ثُمَّ جِيءَ بِجَلِيسِ الْمَلِكِ فَقِيلَ لَهُ: ارْجِعْ عَنْ دِينِكَ، فَأَبَى فَوَضَعَ الْمِئْشَارَ فِي مَفْرِقِ رَأْسِهِ، فَشَقَّهُ بِهِ حَتَّى وَقَعَ شِقَّاهُ، ثُمَّ جِيءَ بِالْغُلَامِ فَقِيلَ لَهُ ارْجِعْ عَنْ دِينِكَ، فَأَبَى فَدَفَعَهُ إِلَى نَفَرٍ مِنْ أَصْحَابِهِ، فَقَالَ: اذْهَبُوا بِهِ إِلَى جَبَلِ كَذَا وَكَذَا، فَاصْعَدُوا بِهِ الْجَبَلَ، فَإِذَا بَلَغْتُمْ ذُرْوَتَهُ، فَإِنْ رَجَعَ عَنْ دِينِهِ، وَإِلَّا فَاطْرَحُوهُ، فَذَهَبُوا بِهِ فَصَعِدُوا بِهِ الْجَبَلَ، فَقَالَ: اللهُمَّ اكْفِنِيهِمْ بِمَا شِئْتَ، فَرَجَفَ بِهِمِ الْجَبَلُ فَسَقَطُوا، وَجَاءَ يَمْشِي إِلَى الْمَلِكِ، فَقَالَ لَهُ الْمَلِكُ: مَا فَعَلَ أَصْحَابُكَ؟ قَالَ: كَفَانِيهِمُ اللهُ، فَدَفَعَهُ إِلَى نَفَرٍ مِنْ أَصْحَابِهِ، فَقَالَ: اذْهَبُوا بِهِ فَاحْمِلُوهُ فِي قُرْقُورٍ، فَتَوَسَّطُوا بِهِ الْبَحْرَ، فَإِنْ رَجَعَ عَنْ دِينِهِ وَإِلَّا فَاقْذِفُوهُ، فَذَهَبُوا بِهِ، فَقَالَ: اللهُمَّ اكْفِنِيهِمْ بِمَا شِئْتَ، فَانْكَفَأَتْ بِهِمِ السَّفِينَةُ فَغَرِقُوا، وَجَاءَ يَمْشِي إِلَى الْمَلِكِ، فَقَالَ لَهُ الْمَلِكُ: مَا فَعَلَ أَصْحَابُكَ؟ قَالَ: كَفَانِيهِمُ اللهُ، فَقَالَ لِلْمَلِكِ: إِنَّكَ لَسْتَ بِقَاتِلِي حَتَّى تَفْعَلَ مَا آمُرُكَ بِهِ، قَالَ: وَمَا هُوَ؟ قَالَ: تَجْمَعُ النَّاسَ فِي صَعِيدٍ وَاحِدٍ، وَتَصْلُبُنِي عَلَى جِذْعٍ، ثُمَّ خُذْ سَهْمًا مِنْ كِنَانَتِي، ثُمَّ ضَعِ السَّهْمَ فِي كَبِدِ الْقَوْسِ، ثُمَّ قُلْ: بِاسْمِ اللهِ رَبِّ الْغُلَامِ، ثُمَّ ارْمِنِي، فَإِنَّكَ إِذَا فَعَلْتَ ذَلِكَ قَتَلْتَنِي، فَجَمَعَ النَّاسَ فِي صَعِيدٍ وَاحِدٍ، وَصَلَبَهُ عَلَى جِذْعٍ، ثُمَّ أَخَذَ سَهْمًا مِنْ كِنَانَتِهِ، ثُمَّ وَضَعَ السَّهْمَ فِي كَبْدِ الْقَوْسِ، ثُمَّ قَالَ: بِاسْمِ اللهِ، رَبِّ الْغُلَامِ، ثُمَّ رَمَاهُ فَوَقَعَ السَّهْمُ فِي صُدْغِهِ، فَوَضَعَ يَدَهُ فِي صُدْغِهِ فِي مَوْضِعِ السَّهْمِ فَمَاتَ، فَقَالَ النَّاسُ: آمَنَّا بِرَبِّ الْغُلَامِ، آمَنَّا بِرَبِّ الْغُلَامِ، آمَنَّا بِرَبِّ الْغُلَامِ، فَأُتِيَ الْمَلِكُ فَقِيلَ لَهُ: أَرَأَيْتَ مَا كُنْتَ تَحْذَرُ؟ قَدْ وَاللهِ نَزَلَ بِكَ حَذَرُكَ، قَدْ آمَنَ النَّاسُ، فَأَمَرَ بِالْأُخْدُودِ فِي أَفْوَاهِ السِّكَكِ، فَخُدَّتْ وَأَضْرَمَ النِّيرَانَ، وَقَالَ: مَنْ لَمْ يَرْجِعْ عَنْ دِينِهِ فَأَحْمُوهُ فِيهَا، أَوْ قِيلَ لَهُ: اقْتَحِمْ، فَفَعَلُوا حَتَّى جَاءَتِ امْرَأَةٌ وَمَعَهَا صَبِيٌّ لَهَا فَتَقَاعَسَتْ أَنْ تَقَعَ فِيهَا، فَقَالَ لَهَا الْغُلَامُ: يَا أُمَّهْ اصْبِرِي فَإِنَّكِ عَلَى الْحَقِّ".
[صحيح] - [رواه مسلم] - [صحيح مسلم: 3005]
المزيــد ...
ከሱሀይብ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል፦
«ከናንተ በፊት ከነበሩት ህዝቦች መካከል አንድ ንጉስ ነበር። ለርሱም ጠንቋይ ነበረው። (ጠንቋዩ) ያረጀ ጊዜም ለንጉሱ እንዲህ አለው: "እኔ አርጅቻለሁ። ጥንቆላ የማስተምረው አንድ ህፃን ልጅ ወደ እኔ ላክልኝ።" ንጉሱም የሚያስተምረውን ህፃን ልጅ ወደርሱ ላከለት። ልጁም ወደ ጠንቋዩ መንገድ ሲጀምር አንድ ባህታዊ ይመለከታል። እርሱ ዘንድም ተቀምጦ ንግግሩን ያዳምጥና ያስደስተዋል። ዘውትር ወደ ጠንቋዩ ዘንድ ሲሄድ በባህታዊው በኩል ሲያልፍ ተቀምጦ አዳምጦ ይሄዳል። ጠንቋዩም (በማርፈዱ) ይመታዋል። ይህንንም ያጋጠመውን ቅሬታ ለባህታዊው ነገረው። ባህታዊውም: "ጠንቋዩ ይመታኛል ብለህ ከፈራህ ቤተሰቤ ነው ያዘገየኝ በለው። ቤተሰብህ ይመቱኛል ብለህ ከፈራህ ደሞ ጠንቋዩ ነው ያዘገየኝ በላቸው።" አለው። በዚህ ሁኔታ ላይ ሳለ አንድ ቀን በመንገዱ ሰዎች እንዳያልፉ መንገድ በዘጋ ትልቅ እንስሳ በኩል አለፈ። እንዲህም አለ: "ጠንቋዩ ነው ትክክለኛ ወይስ ባህታዊው ነው ትክክለኛ የሚለውን ዛሬ ማወቅ እችላለሁ።" ብሎ ድንጋይ አነሳና "አላህ ሆይ! ከጠንቋዩ እምነት ይልቅ የባህታዊው እምነት አንተ ዘንድ ተወዳጅ ከሆነ ሰዎች በመንገዳቸው ያልፉ ዘንድ ይህንን እንስሳ ግደል።" በማለት ወረወረውና ገደለው። ሰዎችም አለፉ። ይህንንም ለባህታዊው ነገረው። ባህታዊውም ይህንን ሲሰማ "ልጄ ሆይ! አንተ ዛሬ ከኔ የተሻልክ ሆነሃል። ጉዳይህ የማየውን ያህል ደርሷልና ትፈተናለህ። ፈተና ሲገጥምህም ወደ እኔ እንዳትጠቁም።" አለው። ልጁም እውሮችንና ለምጣሞችን ይፈውስ፤ ከተለያዩ በሽታዎችም ሰዎችን ያክም ነበር። ይህንንም ታውሮ የነበረ አንድ የንጉሱ አማካሪ ሰማና በርካታ ስጦታዎችን ሸክፎ ወደርሱ በመምጣት "ይህ ሰብስቤ ያመጣሁት ከፈወስከኝ ያንተ ይሆናል።" አለው። ልጁም "እኔ አንድንም ሰው አልፈውስም። የሚፈውሰው አላህ ነው። በአላህ ካመንክ አላህን እለምንልህና ትፈወሳለህ።" አለው። በአላህም አመነ አላህም ፈወሰው። ንጉሱም ዘንድ በመምጣት ከዚህ በፊት ይቀመጥ እንደነበረው ተቀመጠ። ንጉሱም ለርሱ: "አይንህን ማነው የመለሰልህ?" ብሎ ጠየቀው። አማካሪውም: "ጌታዬ" አለው። ንጉሱም: "ከኔ ውጪ ሌላ ጌታ አለህን?" አለው። አማካሪውም: "የኔም ያንተም ጌታ አላህ ነው።" በማለት መለሰለት። ልጁን እስኪጠቁም ድረስም ይዞት ከማሰቃየት አልተወገደም። ልጁም ተይዞ ቀረበ። ንጉሱም በመደነቅ "ልጄ ሆይ! ጥንቆላህ አይነ ስውራንና ለምጣሞችን እስከመፈወስ ደረሰ! ይህንን ሰራህ! ይህንን ሰራህ!" አለው። ልጁም: "እኔ አንድንም አልፈውስም። የሚፈውሰው አላህ ነው።" በማለት መለሰ። ይዞትም ባህታዊውን እስኪጠቁም ድረስ ልጁን ከማሰቃየት አልተወገደም። ባህታዊውም ተይዞ ቀረበ። ለርሱም "ከሃይማኖትህ ውጣ!" ተባለ። እርሱም "በፍፁም!" አለ። መጋዝ አስመጡናና አናቱ መሀል ላይ አስቀመጡት። ከዛም ሁለት ቦታ ከፍለው ጣሉት። ቀጥለው የንጉሱን አማካሪ አቀረቡት። ለርሱም "ከሃይማኖትህ ውጣ!" ተባለ። እርሱም "በፍፁም!" አለ። መጋዝ አናቱ መሀል ላይ አስቀመጠ። ከዛም ሁለት ቦታ ከፍሎ ጣለው። ቀጥለው ልጁን አቀረቡት። "ከሃይማኖትህ ውጣ!" ተባለ። እርሱም "በፍፁም!" አለ። ንጉሱም ልጁን ለተወሰኑ ወታደሮቹ ሰጠና "እርሱን እንዲህ እንዲህ ወደሚባል ተራራ ውሰዱትና ተራራው ላይ ይዛችሁት ውጡ። የተራራው ጫፍ ላይ ስትደርሱ ከሃይማኖትህ ውጣ በሉት። ከተቀበለ አምጡት ካልተቀበለ ወርውሩት።" አላቸው። እርሱንም ወደ ተራራው ይዘውት ወጡ። ልጁም "አላህ ሆይ! በፈለግከው መንገድ ከነርሱ ተንኮል ጠብቀኝ" አለ። ተራራው ተርገፈገፈና ወደቁ። ልጁም ወደ ንጉሱ መጣ። ንጉሱም ለልጁ "ወታደሮቹ ምን ሆኑ?" አለው። ልጁም "አላህ ከነርሱ ተንኮል ጠበቀኝ" አለው። ንጉሱም ለሌሎች ወታደሮች ልጁን ሰጠ። እንዲህም አላቸው: "ልጁን በጀልባ ጭናችሁ ውሰዱት። የባህሩ መሃል ስትደርሱ ከሃይማኖትህ ውጣ በሉት። ከተቀበለ አምጡት ካልተቀበለ ወደ ባህሩ ጣሉት።" ልጁንም ይዘውት ሄዱ። ልጁም "አላህ ሆይ! በፈለግከው መንገድ ከነርሱ ተንኮል ጠብቀኝ" አለ። ጀልባዋ ተገለበጠችና ሰመጡ። ልጁም ወደ ንጉሱ መጣ። ንጉሱም ለልጁ "ወታደሮቹ ምን ሆኑ?" አለው። ልጁም "አላህ ከነርሱ ተንኮል ጠበቀኝ" አለው። አክሎም "እኔ የማዝህን እስካልፈፀምክ ድረስ ልትገለኝ አትችልም" አለው። ንጉሱም: "ምንድነው እርሱ?" አለው። ልጁም "በቅድሚያ ሰዎችን አንድ ሰፊ ሜዳ ላይ ሰብስበህ የዘንባባ ግንድ ላይ ትሰቅለኛለህ። ቀጥሎ ከሰገባዬ ቀስት ትውስዳለህ። ቀጥሎ ቀስቱን ከደጋኑ መሃል ካደረግክ በኋላ "የዚህ ልጅ ጌታ በሆነው በአላህ ስም እወረውራለሁ።" በል። ከዛም ወርውረው። አንተ ይህንን ካደረግክ ትገለኛለህ።" አለው። ንጉሱም ሰዎችን አንድ ሰፊ ሜዳ ላይ ሰበሰበና ልጁን የዘንባባ ግንድ ላይ ሰቀለው። ቀጥሎ ከሰገባው ቀስቱን አወጣና ቀስቱን ደጋኑ መሃል ላይ ካደረገ በኋላ "የዚህ ልጅ ጌታ በሆነው በአላህ ስም እወረውራለሁ።" አለና ወረወረ። ቀስቷም ቅንጡ (ከጆሮው ጎን ያለ አጥንት) ላይ ተሰካች። ልጁም ቀስቱ ያረፈችበትን የጆሮውን ጎን እንደያዘ ሞተ። ሰዎችም "በልጁ ጌታ አምነናል። በልጁ ጌታ አምነናል። በልጁ ጌታ አምነናል።" አሉ። ንጉሱም ጋር በመምጣት እየማሉ "ያ የምትፈራው ነገር ተከሰተብህ አይደል? የምትፈራው ደረሱ፤ ሰዎች አመኑ።" ተባለ። ንጉሱም በመንገድ ዳር ዳር ጉድጓድ እንዲቆፈር አዘዘ። ጉድጓዱም ተቆፈረ። እሳትም ተቀጣጠለ። እንዲህም አለ: "ከሃይማኖቱ ለቆ ያልወጣን። እሳት ውስጥ አቃጥሉት። ወይም እሳት ውስጥ ግባ በሉት።" ህዝቡ ሁሉ አንዲት ህፃን ልጅ የተሸከመች ሴት እስክትቀር ድረስ ንጉሱ እንዳለው እሳት ውስጥ ገቡ። እሳት ውስጥ ለመግባት አመነታች። ያዘለችው ጨቅላ ግን "እናቴ ታገሺ አንቺ እውነት ላይ ነሽ።" አላት።»
[ሶሒሕ ነው።] - [ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 3005]
ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለው ተናገሩ: ከእኛ በፊት ከነበሩት ህዝቦች መካከል አንድ ንጉስ ነበር። ለርሱም አንድ ጠንቋይ ነበረው። ጠንቋዩ ያረጀ ጊዜ ለንጉሱ እንዲህ አለው: "እኔ አርጅቻለሁ። ጥንቆላ የማስተምረውን ብላቴና ወደ እኔ ላክልኝ።" ንጉሱም የሚያስተምረውን ብላቴና ልጅ ወደርሱ ላከለት። ልጁ ወደ ጠንቋዩ መንገድ ሲጀምር መንገድ ላይ አንድ ባህታዊ ነበር። አንድ ቀን እርሱ ዘንድ ተቀምጦ ንግግሩን ያዳምጥና ያስደስተዋል። ዘወትር ወደ ጠንቋዩ ዘንድ ሲሄድ በባህታዊው በኩል ሲያልፍ ተቀምጦ አዳምጦ ይሄዳል። ጠንቋዩም (በማርፈዱ) ይመታዋል። ይህንንም ያጋጠመውን ቅሬታ ለባህታዊው ነገረው። ባህታዊውም: "ጠንቋዩ ይመታኛል ብለህ ከፈራህ ቤተሰቤ ነው ያዘገየኝ በለው። ቤተሰብህ ይመቱኛል ብለህ ከፈራህ ደሞ ጠንቋዩ ነው ያዘገየኝ በላቸው።" አለው። በዚህ ሁኔታ ላይ ሳለ አንድ ቀን ሰዎች እንዳያልፉ መንገድ በዘጋ ትልቅ እንስሳ በኩል አለፈ። እንዲህም አለ: "ዛሬ ጠንቋዩ ነው ትክክለኛ? ወይስ ባህታዊው ነው ትክክለኛ? የሚለውን አውቃለሁ።" ድንጋይም አነሳና "አላህ ሆይ! ከጠንቋዩ እምነት ይልቅ የባህታዊው እምነት አንተ ዘንድ ተወዳጅ ከሆነ ሰዎች በመንገዳቸው ያልፉ ዘንድ ይህንን እንስሳ ግደል።" በማለት ወረወረውና ገደለው። ሰዎችም አለፉ። ይህንንም ለባህታዊው ነገረው። ባህታዊውም ለርሱ እንዲህ አለው: "ልጄ ሆይ! አንተ ዛሬ ከኔ የተሻልክ ሆነሃል። ጉዳይህ የማየውን ያህል ደርሷልና ትፈተናለህ። ፈተና ሲያጋጥምህም ወደ እኔ እንዳትጠቁም።" አለው። ልጁም እውሮችንና ለምጣሞችን ይፈውስ ጀመር። በአላህ ፍቃድም ከተለያዩ በሽታዎችም ሰዎችን ያክም ነበር። ይህንንም ታውሮ የነበረ አንድ የንጉሱ አማካሪ ሰማና በርካታ ስጦታዎችን ሸክፎ ወደርሱ በመምጣት እንዲህ አለው: "ይህ ሰብስቤ ያመጣሁት ከፈወስከኝ ያንተ ይሆናል።" ልጁም "እኔ አንድንም ሰው አልፈውስም። የሚፈውሰው አላህ ነው። በአላህ ካመንክ አላህን እለምንልህና ትፈወሳለህ።" አለው። በአላህም አመነ አላህም ፈወሰው። ንጉሱም ዘንድ በመምጣት ከዚህ በፊት ይቀመጥ እንደነበረው ተቀመጠ። ንጉሱም ለርሱ: "አይንህን ማነው የመለሰልህ?" ብሎ ጠየቀው። አማካሪውም: "ጌታዬ" አለው። ንጉሱም: "ከኔ ውጪ ሌላ ጌታ አለህን?" አለው። አማካሪውም: የኔም ያንተም ጌታ አላህ ነው።" በማለት መለሰ። ልጁን እስኪጠቁም ድረስም ይዞት ከማሰቃየት አልተወገደም። ልጁም ተይዞ ቀረበ። ንጉሱም በመደነቅ እንዲህ አለው: "ልጄ ሆይ! ጥንቆላህ አይነ ስውራንና ለምጣሞችን እስከመፈወስ ደረሰ ማለት ነዋ! ይህንን ሰራህ! ይህንን ሰራህ!" ልጁም: "እኔ አንድንም አልፈውስም። የሚፈውሰው አላህ ነው።" በማለት መለሰ። ይዞትም ባህታዊውን እስኪጠቁም ድረስ ልጁን ከማሰቃየት አልተወገደም። ባህታዊውም ተይዞ ቀረበ። ለርሱም "ከሃይማኖትህ ውጣ!" ተባለ። እርሱም "በፍፁም!" አለ። መጋዝ አስጠሩና አናቱ መለያ ጋር አስቀመጡት። ከዛም ለሁለት ሰንጥቀው ጣሉት። ቀጥለውም የንጉሱን አማካሪ አቀረቡት። ለርሱም "ከሃይማኖትህ ውጣ!" ተባለ። እርሱም "በፍፁም!" አለ። መጋዝ አናቱ መለያ ጋር ተደረገና ለሁለት ተሰንጥቆ ወደቀ። ቀጥለውም ልጁን አቀረቡት። "ከሃይማኖትህ ውጣ!" ተባለ። እርሱም "በፍፁም!" አለ። ንጉሱም ልጁን ከሶስት እስከ አስር ለሚጠጉ ወታደሮቹ አሳልፎ ሰጠው። "እርሱን እንዲህ እንዲህ ወደሚባል ተራራ ውሰዱትና ተራራው ላይ ይዛችሁት ውጡ። የተራራው ጫፍ ላይ ስትደርሱ ከሃይማኖትህ ውጣ በሉት። ከተቀበለ አምጡት ካልተቀበለ ወርውሩት።" አላቸው። እርሱንም ወደ ተራራው ይዘውት ወጡ። ልጁም "አላህ ሆይ! በፈለግከው መንገድ ከነርሱ አንተው ብቃኝ።" አለ። ተራራው ተርገፈገፈ፣ ሀይለኛ መንቀጥቀጥ ተንቀጥቅጦ ወደቁ። ልጁም ወደ ንጉሱ መጣ። ንጉሱም ለልጁ "ወታደሮቹ ምን ሆኑ?" አለው። ልጁም "አላህ ከነርሱ ተንኮል ጠበቀኝ" አለ። ንጉሱም ለሌሎች ወታደሮች ልጁን ሰጠ። እንዲህም አላቸው: "ልጁን በጀልባ ጭናችሁ ውሰዱት። የባህሩ መሃል ስትደርሱ ከሃይማኖትህ ውጣ በሉት። ከተቀበለ አምጡት ካልተቀበለ ወደ ባህሩ ጣሉት።" ልጁንም ይዘውት ሄዱ። ልጁም "አላህ ሆይ! በፈለግከው መንገድ ከነርሱ ተንኮል ጠብቀኝ።" አለ። ጀልባዋ ተገለበጠችና ሰመጡ። ልጁም ወደ ንጉሱ መጣ። ንጉሱም ለልጁ "ወታደሮቹ ምን ሆኑ?" አለው። ልጁም "አላህ ከነርሱ ተንኮል ጠብቀኝ።" አለው። አክሎም "አንተ እኔ የማዝህን እስካልፈፀምክ ድረስ ልትገለኝ አትችልም።" አለው። ንጉሱም: "ምንድነው እርሱ?" አለው። ልጁም "በቅድሚያ ሰዎችን አንድ ገላጣ ሜዳ ላይ ሰብስበህ የዘንባባ ግንድ ላይ ትሰቅለኛለህ። ቀጥሎ ከሰገባዬ ቀስት ትውስዳለህ። ቀጥሎ ቀስቱን ከደጋኑ መሃል ካደረግክ በኋላ 'የዚህ ልጅ ጌታ በሆነው በአላህ ስም እወረውራለሁ።' በል። ከዛም ወርውረው። አንተ ይህንን ካደረግክ ትገለኛለህ።" አለው። ንጉሱም ሰዎችን አንድ ሜዳ ላይ ሰበሰበና ልጁን የዘንባባ ግንድ ላይ ሰቀለው። ቀጥሎ ከሰገባው ቀስቱን አወጣና ቀስቱን ደጋኑ መሃል ላይ ካደረገ በኋላ "የዚህ ልጅ ጌታ በሆነው በአላህ ስም እወረውራለሁ።" አለና ወረወረ። ቀስቷም በአይኑና በጆሮው መካከል ቅንጡ ላይ ተሰካች። ልጁም ቀስቱ ያረፈችበትን የጆሮውን ጎን እንደያዘ ሞተ። ሰዎችም "በልጁ ጌታ አምነናል። በልጁ ጌታ አምነናል። በልጁ ጌታ አምነናል።" አሉ። ንጉሱም ጋር በመምጣት "አየህ ያ የምትፈራውን ነገር? ያለ ጥርጥር ተከሰተብህ። ይሀውም ሰዎች ልጁን ተከትለው ሁሉም በጌታቸው አመኑ።" ተባለ። ንጉሱም በየመንገድ ዳር ዳር ትልቅና ረጃጅም ጉድጓድ እንዲቆፈር አዘዘ። ጉድጓዱም ተቆፈረ። እሳትም በውስጡ ተቀጣጠለ። እንዲህም አለ: "ከሃይማኖቱ ለቆ ያልወጣን። እሳት ውስጥ ጣሉትና አቃጥሉት።" ህዝቡ ሁሉ አንዲት ህፃን ልጅ የተሸከመች ሴት እስክትቀር ድረስ ንጉሱ እንዳለው እሳት ውስጥ ተወረወረ። እሳት ውስጥ ለመግባት አመነታች። ቦታዋን እንደያዘች ቆመች። እሳት ውስጥ መግባቱን ጠላች። ያዘለችው ጨቅላ ግን እንዲህ አላት: "እናቴ ታገሺ አንቺ እውነት ላይ ነሽ።"