+ -

عَنْ أبي سَعيدٍ الخُدريَّ رضي الله عنه قال: قال رسولُ الله صلَّى الله عليه وسلم ِ:
«إزْرَةُ المُسْلمِ إلى نصفِ السَّاق، وَلَا حَرَجَ -أو لا جُنَاحَ- فيما بينَهُ وبينَ الكعبينِ، وما كان أسفلَ منَ الكعبين فهو في النار، مَن جرَّ إزارَهُ بطرًا لم يَنْظُرِ اللهُ إليه».

[صحيح] - [رواه أبو داود وابن ماجه وأحمد] - [سنن أبي داود: 4093]
المزيــد ...

ከአቡ ሰዒድ አልኹድሪይ -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንዲህ አሉ፦ «የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ ብለዋል፦
"የሙስሊም ሽርጥ እስከ ባቱ ግማሽ ድረስ ነው። ከባቱ ግማሽና በቁርጭምጭሚቱ መሃል ቢሆንም ግን ችግር የለውም። ከቁርጭምጭሚት ዝቅ ያለ ከሆነ እርሱ እሳት ውስጥ ነው። ሽርጡን በኩራት የጎተተን ሰው አላህ ወደርሱ አይመለከትም።"

[ሶሒሕ ነው።] - [አቡዳውድ፣ ኢብኑ ማጀህና አሕመድ ዘግበውታል።] - [ሱነን አቡዳውድ - 4093]

ትንታኔ

ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) አንድ ወንድ ሙስሊም ሽርጡን ምን ማድረግ እንዳለበት ገለፁ። ሽርጥ ሲባል (በዚህ አገባቡ) የወንድን ከወገብ በታች የሚሸፍን የሆነ ልብስ ሁሉ የሚመለከት ነው። ይህም ሶስት ሁኔታዎች አሉት: የመጀመሪያው: ተወዳጅ የሆነ ነው። ይህም እስከ ባቱ ግማሽ ድረስ አሳጥሮ ማድረግ ነው። ሁለተኛው: ሳይጠላ የሚፈቀድ ነው። ይህም ከባቱ ግማሽ በታች እስከ ቁርጭምጭሚቱ ድረስ ባለው አሳጥሮ ማድረጉ ነው። ቁርጭምጭሚት ማለት በባትና እግር መካከል የሚለየው እብጥ ያሉት አጥንቶች ናቸው። ሶስተኛው: ክልክል የሆነው ነው። ይህም ከቁርጭምጭሚት በታች መሆኑ ነው። ይህም እሳት እንዳያገኘው ይፈራለታል። ከቁርጭምጭሚቱ በታች ያስረዘመው በኩራት፣ በመመፃደቅና በጥመት ከሆነ ደግሞ አላህ ወደርሱ አይመለከትም።

ትርጉም: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ስፔንኛ ኢንዶኔዥያኛ ባንጋሊኛ ፈረንሳይኛ ቱርክኛ ቦስንያኛ ሲንሃላዊ ህንድኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ቬትናማዊ ታጋሎግ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ስዋሒልኛ ታይላንድኛ አሳምኛ الهولندية الغوجاراتية
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. ይህ ባህሪና ዛቻ በወንዶች ላይ ብቻ የተገደበ ነው። ሴቶች እዚህ ውስጥ አይካተቱም። ምክንያቱም እነርሱ ሰውነታቸውን ባጠቃላይ እንዲሸፍኑ የታዘዙ ስለሆኑ ነው።
  2. የወንድን ከወገብ በታች የሚሸፍን የሆነ ልብስ ሁሉ "ኢዛር" ተብሎ ይጠራል። እንደሱሪና ሌሎች ልብሶች ይመስል። እነዚህ ሁሉ ልብሶች እዚህ ሐዲሥ ውስጥ የተጠቀሰው ሸሪዓዊ ህግጋት ውስጥ ይገባሉ።