عَنْ أَنَسٍ رَضيَ اللهُ عنه قَالَ: قَالَ رَسُولُ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ:
«لَوْ كَانَ لِابْنِ آدَمَ وَادِيَانِ مِنْ مَالٍ لَابْتَغَى وَادِيًا ثَالِثًا، وَلَا يَمْلَأُ جَوْفَ ابْنِ آدَمَ إِلَّا التُّرَابُ، وَيَتُوبُ اللهُ عَلَى مَنْ تَابَ».
[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح مسلم: 1048]
المزيــد ...
አነስ ቢን ማሊክ -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና- እንዳስተላለፉት እንዲህ ብለዋል: «የአላህ መልክተኛ -የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - እንዲህ ብለዋል፦
"የአደም ልጅ ሁለት በገንዘብ የሞላ ሸለቆ ቢኖረው ኖሮ ሶስተኛ ሸለቆ ይመኛል። የአደምን ልጅ ሆድ ከአፈር በቀር የሚሞላው የለም። ወደ አላህ ተፀፅቶ በተመለሰ ሰው ላይም አላህ ተውበቱን ይቀበለዋል።"»
[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 1048]
ነቢዩ -የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - የአደም ልጅ በወርቅ የሞላ ሸለቆ ቢኖረው ኖሮ በተፈጥሮው ካለው ስግብግብነት አንፃር ሌሎች ሁለት ሸለቆዎችን ይመኝ ነበር። የአደም ልጅ ሙቶ ከርሱ በቀብሩ አፈር ካልሞላ በቀር ለዱንያ ስግብግብ ከመሆን አይወገድም።