+ -

عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ رضي الله عنه أَنَّ رَسُولَ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ قَالَ يَوْمَ خَيْبَرَ:
«لَأُعْطِيَنَّ هَذِهِ الرَّايَةَ رَجُلًا يُحِبُّ اللهَ وَرَسُولَهُ، يَفْتَحُ اللهُ عَلَى يَدَيْهِ» قَالَ عُمَرُ بْنُ الْخَطَّابِ: مَا أَحْبَبْتُ الْإِمَارَةَ إِلَّا يَوْمَئِذٍ، قَالَ فَتَسَاوَرْتُ لَهَا رَجَاءَ أَنْ أُدْعَى لَهَا، قَالَ فَدَعَا رَسُولُ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ عَلِيَّ بْنَ أَبِي طَالِبٍ، فَأَعْطَاهُ إِيَّاهَا، وَقَالَ: «امْشِ، وَلَا تَلْتَفِتْ، حَتَّى يَفْتَحَ اللهُ عَلَيْكَ» قَالَ فَسَارَ عَلِيٌّ شَيْئًا ثُمَّ وَقَفَ وَلَمْ يَلْتَفِتْ، فَصَرَخَ: يَا رَسُولَ اللهِ، عَلَى مَاذَا أُقَاتِلُ النَّاسَ؟ قَالَ: «قَاتِلْهُمْ حَتَّى يَشْهَدُوا أَنْ لَا إِلَهَ إِلَّا اللهُ وَأَنَّ مُحَمَّدًا رَسُولُ اللهِ، فَإِذَا فَعَلُوا ذَلِكَ فَقَدْ مَنَعُوا مِنْكَ دِمَاءَهُمْ وَأَمْوَالَهُمْ، إِلَّا بِحَقِّهَا وَحِسَابُهُمْ عَلَى اللهِ».

[صحيح] - [رواه مسلم] - [صحيح مسلم: 2405]
المزيــد ...

ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና የኸይበር ቀን እንዲህ አሉ:
«"አላህና መልክተኛውን ለሚወድ፣ አላህም በእጁ ድልን የሚያጎናፅፈው ለሆነ አንድ ሰው ይህንን ባንዲራ እሰጣለሁኝ።" ዑመር ቢን አልኸጧብ እንዲህ አሉ: "ከዚያ ቀን ውጭ ሹመትን ወድጄ አላውቅም። ለርሷ እንድጠራ በመከጀልም ተንጠራራሁኝ።" የአላህ መልክተኛም (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ዐሊይ ቢን አቢ ጧሊብን ጠርተው ባንዲራውን ሰጡት። እንዲህም አሉት "አላህ ባንተ ላይ ድልን እስኪያጎናፅፍ ሳትዞር ተጓዝ።" ዐሊይ ጥቂት ተጓዘ ከዚያም ሳይዞር ቆም አለና ጮኽ ብሎ "የአላህ መልክተኛ ሆይ! ሰዎቹን በምን ላይ ነው የምዋጋው?" አላቸው። እርሳቸውም "ከአላህ በቀር በእውነት የሚመለክ እንደሌለና ሙሐመድም የአላህ መልክተኛ መሆናቸውን እስኪመሰክሩ ተዋጋቸው። ይህንን ከፈፀሙ ደማቸውንና ገንዘባቸውን በሐቁ ካልሆነ በቀር ከአንተ ተከላክለዋል። ሒሳባቸው ግን አላህ ዘንድ ነው።" አሉ።»

[ሶሒሕ ነው።] - [ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 2405]

ትንታኔ

ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ነገ በመዲና አቅራቢያ በምትገኘው የኸይበር ከተማ አይሁዶች ላይ ሙስሊሞች ድልን እንደሚያገኙ ለሶሐቦች ተናገሩ። ይህም ባንዲራውን በሚሰጡት ሰው እጅ ነው። ባንዲራ ማለት ለመታወቂያነት ሰራዊቱ የሚይዘው ምልክት ነው። ይህ ሰው ከባህሪዎቹ መካከል አላህና መልክተኛውን ይወዳል፤ አላህና መልክተኛውም ይወዱታል።
ዑመር ቢን አልኸጣብም (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - ከዛ ቀን በቀር ሹመትን እንዳልወደዱና አላማ አድርገው እንዳልያዙ አወሱ። ይህም ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና አላህና መልክተኛውን ይወዳል ብለው ያወሱትን መገለጫ ለማግኘት በመከጀል ነው። ዑመር (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና አይተውት እንዲጠሩት ይህንንም ባንዲራ ለመያዝ በመጓጓትና በመከጀል ተንጠራሩ።
ነቢዩም (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ዐሊይ ቢን አቢ ጧሊብን (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - ጠርተው ባንዲራውን ሰጡት። ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ሰራዊቱን ይዞ እንዲንቀሳቀስ፤ ጠላቶቹን ከተገናኘ በኋላም ምሽጎቹን በድልና በማሸነፍ አላህ እስኪከፍትለት ድረስ በእረፍትም ይሁን ወይ በማቆም አለበለዚያም በስምምነት ምክንያት ጦርነቱን እንዳያቆም አዘዙት።
ዐሊይም (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራውን ይውደድላቸውና - ተጓዙ ከዚያም የነቢዩን (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ትእዛዝ ላለመፃረር ሳይዞሩ ቆም ብለው ድምፃቸውን ከፍ በማድረግ "የአላህ መልክተኛ ሆይ! ሰዎቹን በምን ላይ ነው የምዋጋቸው?" አሉ።
ነቢዩም (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና "ከአላህ በቀር በእውነት የሚመለክ እንደሌለና ሙሐመድም የአላህ መልክተኛ መሆናቸውን እስኪመሰክሩ ተዋጋቸው። ይህን ተቀብለው ወደ እስልምና ከገቡ ደምና ገንዘባቸውን ከአንተ ተከላክለዋል። በአንተም ላይ እርም ተደርጓል። በሐቁ ካልሆነ በቀር ማለትም በእስልምና ህግጋት መሰረት በርሱ ሊገደሉበት የሚገባቸውን ወንጀል ወይም ግድያ እስካልፈፀሙ ድረስ እንዳትገድላቸው ማለት ነው። ሒሳባቸው ታዲያ አላህ ዘንድ ነው።

ትርጉም: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ስፔንኛ ኢንዶኔዥያኛ ኡይጙራዊ ፈረንሳይኛ ቱርክኛ ሩስያኛ ቦስንያኛ ሲንሃላዊ ህንድኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ቬትናማዊ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ማላያላምኛ ስዋሒልኛ ታይላንድኛ ቡሽትኛ አሳምኛ الهولندية الغوجاراتية الرومانية Oromisht
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. ሹመት ትልቅ ተጠያቂነት ስላለው ሶሐቦች ይጠሉት ነበር።
  2. መልካምነቱ የተረጋገጠ ለሆነ ነገር ራስን ማጨትና ብቅ ብቅ ማለት እንደሚፈቀድ እንረዳለን።
  3. መሪ የሆነ ሰው ለሰራዊት ቡድኑ መሪ በጦር አውድማ ውስጥ በምን መልኩ እንደሚዋጋ አቅጣጫ እንደሚሰጥ እንረዳለን።
  4. የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ባልደረቦች የርሳቸውን ትእዛዝ ለመፈፀም በመቻኮል ላይ ያላቸውን ጥንካሬ እንረዳለን።
  5. ከታዘዘው ነገር አንዳች የተወሳሰበበት ሰው ስለርሱ መጠየቅ እንደሚገባው እንረዳለን።
  6. ከነቢይነታቸው ምልክት መካከል በየሁዶች ላይ የኸይበርን መከፈት ድል እንደሚጎናፀፉ ተናግረው እንደተናገሩት መከሰቱ ነው።
  7. የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ወዳዘዙት ትእዛዝ ቀድሞ መገኘትና መቻኮል ላይ መነሳሳቱን እንረዳለን።
  8. ግድያን የሚያስገድዱ ነገሮች ግልፅ እስካልሆኑበት ድረስ ሁለቱን የምስክር ቃላት የተናገረን ሰው መግደል እንደማይፈቀድ እንረዳለን።
  9. የእስልምና ህግጋት ተፈፃሚ የሚሆነው ለሰዎች ግልፅ በሆነ ነገር ላይ ነው። የውስጣቸውንማ ሀላፊነት የሚወስደው አላህ ነው።
  10. የጂሃድ ትልቁ አላማ ሰዎችን ወደ እስልምና እንዲገቡ ማድረግ ነው።
ተጨማሪ